ቪዲዮዎች (130 Videos)
በቴሌግራም ቻናላችን ከተለቀቁ 2024 - 2026 ሙሉ አጫጭርና ረጅም ትምህርታዊ ቪዲዮዎች መሐከል የተመረጡትን እዚህ ይመልከቱ።
ተጨማሪ የቪዲዮ ፋይሎች (Additional Videos)
★ጌታዬ ያኔ ሲጠይቀኝ እያለ " ምነው ማታፍር አንተ እኔን ስታምፀኝ"★~~አማሙ አህመድን ያስለቀሰ ልብ የሚነካ ግጥምትርጉም...
★ጌታዬ ያኔ ሲጠይቀኝ እያለ " ምነው ማታፍር አንተ እኔን ስታምፀኝ"★~~አማሙ አህመድን ያስለቀሰ ልብ የሚነካ ግጥምትርጉም#ኡስታዝ_ኢብኑ_ሙነወር→ጌታዬ ያኔ ሲጠይቀኝ→እያለ " ምነው ማታፍር አንተ እኔን ስታምፀኝ"→"ከፍጡሮቼ ሁሉ ወንጀልህን እየሸሸግክ→እኔ ጋር ግን መጣህ አመፅክን ተሸክመክ"→ወይኔ! ምን ይውጠኛል→ማንስ ይጠብቀኛል→ጊዜ ሄዶ አልፎ ጊዜ ሲተካ→ነፍሴ በምኞት ሲረካ→ዘነጋሁ የወዲያኛውን→ከሞት ከፈኔ የሚከተለውን→ዘላለም ለመኖር ቃል እንደተገባልኝ→ሞት የሚባል ነገር እንደማይመጣብኝ→ይሄው ጣእረ–ሞት መጣ→ማን ያተርፈኛል ከዚህ ጣጣ?→ዙርያየ ያሉን ቃኘሁኝ→የሚጠቅመኝ ግን አጣሁኝ→ምን እንዳስቀደምኩ ልጠየቅ ነኝ→ለዚህ ግዜየ የሚሆነኝ→ያኔ ምን ይሆን መልሴ→በእምነቴ ችላ ያልኩትን እራሴ→ወይኔ! ከቶ ምን ይብቃኝ→ሰምቼ አልነበርን የጌታዬ ቃል ሲጠራኝ?→በቃፍም፣በያሲን ያለውን→ምነው አልሰማሁ ተግሳፁን→ምነው አልሰማሁ ትንሳኤውን→የፍርዱን ቀንና መሰብሰቡን?→መለከል–መውት ሲፈልገኝ→አልሰማሁም ወይ ሲጠራኝ?→ጌታ ሆይ! እኔ ባሪያህ ተመለስኩኝ→ማን አለ ከለላ የሚሰጠኝ→ከምሕረተ ሰፊው ጌታ ሌላ→እኔን ወደ ሀቅ የሚመራ→በንሰሐ መጣሁ ይቅር በለኝ→መልካም ሚዛኔን አክብድልኝ→ሒሳቤን አርገው ቀና→ተስፋዬ አንተው ነህና~~
ከደጋግ ሰለፎቻችን የዱንያ እሳት ሲመለከቱ የኣኺራዉን እሳት አስታዉሶቸዉእራሳቸዉን ስተዉ የሚወድቁነበሩ ይህ እንግዲህ በኢባ...
ከደጋግ ሰለፎቻችን የዱንያ እሳት ሲመለከቱ የኣኺራዉን እሳት አስታዉሶቸዉእራሳቸዉን ስተዉ የሚወድቁነበሩ ይህ እንግዲህ በኢባዳ ትጉ አላህን የሚፈሩ ከመሆናቸዉ ጋር ነዉ እኛ ደግሞ የወንጀል በሀር ዉስጥ እየዋኘን ብዙ ጊዜያችንን በሶሻል ሚድያዉ በሳቅ በጫዋታ በዛዛታ እናሳልፉለን አላህ ይድረስልን ።قال الله تعالى : {اقْتَرَبَ لِلنَّاسِ حِسَابُهُمْ وَهُمْ فِي غَفْلَةٍ مُّعْرِضُونَ}{ለሰዎች እነርሱ በዝንጋቴ ውስጥ (መሰናዳትን) የተው ኾነው ሳሉ ምርመራቸው ቀረበ፡፡}#እኛስ5http://t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
መለከል መውት የዱንያ ቆይታውን ለማገባደድ ጥቂት ሴኮንዶች የቀረውን ፍጡር ከሌሎች ነጥሎ ለመውሰድ ባሻው መንገድ ይመጣል። ...
መለከል መውት የዱንያ ቆይታውን ለማገባደድ ጥቂት ሴኮንዶች የቀረውን ፍጡር ከሌሎች ነጥሎ ለመውሰድ ባሻው መንገድ ይመጣል። ይህ ክስተት «ሟች ይህን ቢያደርግ ኖሮ ይህ አይፈጠርም ነበር» የሚል ክፍተት እንደሌለው የሩቅ ምስጢራት ግርዶ ላልተገለጠልን የመሬት ነዋሪዎች መማሪያ ነው። ቀለሙ ተነስቷል ፤ ወረቀቱም ደርቋል።=t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
🛑 ወንጀሌ በዝቷል እጅግ በጣም ጨንቆኛል አላህ ግን ይቅር ይለኝ ይሁን ???⭐️አዎን በሚገባ ተዉበት አድርግ እንጂ እጅግ ...
🛑 ወንጀሌ በዝቷል እጅግ በጣም ጨንቆኛል አላህ ግን ይቅር ይለኝ ይሁን ???⭐️አዎን በሚገባ ተዉበት አድርግ እንጂ እጅግ በጣም ሩህሩህ አዛኝ የሆነዉ አላህ ይቅር ይልሃል አብሽር ከአንተ የባሱትንም ከልባቸዉ ወደ እርሱ ተመልሰዉ ይቅር ብሎዋቸዋል 100 ሰዉ ገድሎ ከልቡ ወደ ጌታዉ በመመለሱ ይቅር የተባለዉን ሰዉ ታሪክ እየሰማህ ለምን ተስፋ ትቆርጣለህ ???በፍጹም አትቁረጥ ሸይጣን አይጫወትብህ ወንድሜ ወንጀል ዉስጥ ከጣለህ አንተ ደግሞ ወደ አላህ በመመለስ አንገቱን አስደፋዉ ።እዝነተ ሰፊዉ ጌታችን በተከበረዉ መፅሀፉ እንዲህ ይላል :۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُበላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡
ኢማም ኢብኑል ጀውዚ ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ አሉ፡-«የትናንት ደስታ የት አለ?! ሄዷል፣ ፀፀትን ብቻ ትቶ!የነፍስ ስሜትስ...
ኢማም ኢብኑል ጀውዚ ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ አሉ፡-«የትናንት ደስታ የት አለ?! ሄዷል፣ ፀፀትን ብቻ ትቶ!የነፍስ ስሜትስ የት አለ? ስንት ጭንቅላቶችን ዝቅ አስደርጓል፣ ስንት እግሮችንም አሳስቷል!የተሳካለት ሰው የተሳካለት በስሜቱ ተቃራኒ በመሆን እንጂ በሌላ አይደለም። የተሸወደ ሰውም የተሸወደው ዱንያውን በመምረጥ እንጂ በሌላ አይደለም።»✅ለፍተቱል ከቢድ ፊ ነሲሀቲል ወለድ (3)
~የድብቅ ወንጀሎች ልብን ያደርቃሉ፣ የኢማንን ብርሃን ያደበዝዛሉ። በሰው ፊት እንደ ንጹህ በግ መስለው፣ በስውር ግን እንደ...
~የድብቅ ወንጀሎች ልብን ያደርቃሉ፣ የኢማንን ብርሃን ያደበዝዛሉ። በሰው ፊት እንደ ንጹህ በግ መስለው፣ በስውር ግን እንደ ተኩላ የሚያደቡ ሰዎች መጨረሻቸው ውርደት ነው። ምክንያቱም አላህ ሁሉን አዋቂ ነውና የደበቁትን ሁሉ በቂያማ ቀን አደባባይ ያወጣዋል። በዚያች አስፈሪ ቀን፣ ምላስና እጆች ሲመሰክሩ፣ በሌሊት የተሸመነው የኃጢአት ድር ሁሉ ይተረተራል።በእርግጥም ከሰዎች ለመደበቅ የሚደረገው ጥረት፣ ከአላህ ለመደበቅ ከሚደረገው ጥረት ጋር ሲነጻጸር ምንኛ ኢምንት ነው! የሰው ልጅ እይታ ውስን ነው፣ እውቀቱም የተወሰነ ነው። የአላህ እውቀት ግን ሁሉን ከባቢ ነው። ስለዚህ ወንድሜ/እህቴ ሆይ፣ በሰው ፊት መልካም ለመባል ሳይሆን፣ በጌታህ ፊት ንጹህ ለመሆን ተጣጣር። በድብቅ የምትሰራው መልካም ስራ እንደሚያስደስተው ሁሉ፣ በስውር የምትፈፅመውን ኃጢአትም እንደሚያስቆጣው እወቅ። ልብህ ሁሌም በአላህ እይታ ስር መሆኑን ያስታውስ፤ ያኔ መተናነስህ ከፍ ይላል፣ ስራህም ያማረ ይሆናል።t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
🎙«ከቀልቦች ጋር»አዲስ የፖድካስት ፕሮግራም!በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው «ከቀልቦች ጋር...!» የተሰኘው አዲስ የፖድካስት ፕ...
🎙«ከቀልቦች ጋር»አዲስ የፖድካስት ፕሮግራም!በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው «ከቀልቦች ጋር...!» የተሰኘው አዲስ የፖድካስት ፕሮግራማችን እነሆ የፊታችን እሁድ መስከረም 25 ሊደርስዎ ዝግጅቱን አጠናቋል።🤍በዚህ ልዩ ዝግጅታችን ላይ፦✔️ኡስታዝ አቡ ዓቲካ✔️ኡስታዝ ዓብዱ ረዛቅ✔️ኡስታዝ አቡ ሱፍያን📝ከእናንተው ከተከታዮቻችን ለተነሱ ከቀልብ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ምላሽና መፍትሄ በ አላህ ፍቃድ ይሰጣሉ። ከቀልብ ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች ላይ ጥልቅ ውይይትን ያደርጋሉ።📆ቀን፡እሁድ፣ መስከረም 25🕑ሰዓት፡ከ3:30 ብኃላ😂ቀጥታ ስርጭት አድራሻ፡👇https://t.me/Sle_qelbachn1https://t.me/Sle_qelbachn1
ሸይኽ አብዱረዛቅ አል-በድር «አዳእ ወደዋእ» የተሰኘውን ኪታብ አስፈላጊነት አስመልክተው ሲናገሩ እንድህ ይላሉ፦«አንተ ወ...
ሸይኽ አብዱረዛቅ አል-በድር «አዳእ ወደዋእ» የተሰኘውን ኪታብ አስፈላጊነት አስመልክተው ሲናገሩ እንድህ ይላሉ፦«አንተ ወጣት ሆይ! ይህ ኪታብ ገና በወጣትነትህ ጊዜ በእጅህ መገኘቱ አላህ በ አንተ ላይ ከዋለልህ ጸጋዎች አንዱ ነው።በማስተንተን፣በማስተዋል አንብበው፤በአላህ ፈቃድ በሕይወትህ ላይ ታላቅ ተጽእኖ ይኖረዋል።»―|•|t.me/Sle_qelbachn1
ዝሙት (ዚና) በእርግጥም ብድር ነው። ይህን ዕዳ አንተ ከፈጸምከው (ካበደርከው)፣ ክፍያው ከቤተሰብህ ዘንድ ይሆንብሃል።እወ...
ዝሙት (ዚና) በእርግጥም ብድር ነው። ይህን ዕዳ አንተ ከፈጸምከው (ካበደርከው)፣ ክፍያው ከቤተሰብህ ዘንድ ይሆንብሃል።እወቅ! በአንዲት ሴት ላይ በሁለት ሺህ ዲርሃም ዝሙት የፈፀመ ሰው፥ በቤቱ ውስጥ ያለ ዲርሃም ዝሙት እንደሚፈፀምበት ዕወቅ!»t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
ራስን በራስ ማርካት!–ክፍል 1―~በርግጥም የምንኖርበት ዘመን ከባድ ነው። ቴክኖሎጂው የመጣው ህይወትን ሊያቀል ነበር፤ ነገ...
ራስን በራስ ማርካት!–ክፍል 1―~በርግጥም የምንኖርበት ዘመን ከባድ ነው። ቴክኖሎጂው የመጣው ህይወትን ሊያቀል ነበር፤ ነገር ግን ሰይጣን ለክፉ ተጠቅሞበት በጣትህ ጫፍ በሚነካ ስክሪን አማካኝነት ወደ መኝታህ ገብቷል። ዛሬ ላይ ብዙ ወጣቶች በድብቅ የሚያለቅሱበት፣ ከሰው ተደብቀው አንገት የሚደፉበት፣ የህሊና እረፍት ያጡበት ትልቁ በሽታ«ኢስቲምናእ» (ራስን በራስ ማርካት)አንዱና ትልቁ የወጣቱ ችግር ነው።ይህ ተግባር ዝም ብሎ መጥፎ ልማድ ብቻ አይደለም፤ የወጣትነትን ወዝ የሚጠጣ፣ ከአላህ የሚያጣላ፣ የነገን ተስፋ የሚያጨልም «የድብቅ ካንሰር» ነው። እስቲ ቆም ብለህ ተመልከት! ጌታችን አላህ የሰው ልጅን ሲፈጥር ክብር ሰጥቶታል። ስሜትንም የሰጠህ ለተፈቀደ ትዳርና ለዘር መተካት እንጂ በእጅህ ልትጫወትበት አይደለም። በቁርኣን ውስጥ አማኞችን ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-«እነዚያም እነሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ናቸው፡፡ በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙት (ባሮች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ ከዚያም ወዲያ (ሌላን) የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነሱ ወሰን አላፊዎቹ ናቸው፡፡»(ሱረቱ አል-ሙእሚኑን 5-7)ከዚህ አያ መረዳት እንደምንችለው ከትዳር ውጪ ስሜትን ማውጣት «ወሰን አላፊነት» ነው። ነብያችን(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወጣቶችን አግብተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ፣ ካልቻሉ ደግሞ እንዲጾሙ አዘዋል እንጂ ራስን በራስ ማርካትን አልፈቀዱም።ውድ ወንድሜ! ስሜትህን በተከለከለ መንገድ ባወጣህ ቁጥር፣ ከአላህ እዝነት ትርቃለህ። ዱዓህ እንዳይሰምር፣ ዒባዳህ እንዳይጣፍጥህ የሚያደርገው ይሄው የረከሰ ተግባር ነው።አላህ የሰጠህን የተከበረ አካል ማርከስ በእስልምና የተጠላ ተግባር ነው።ከ አላህ ጋር ከማጣላቱ ባሻገር ይህ ሱስ ከአደንዛዥ ዕፅ ባልተናነሰ በአእምሮ ላይ ከባድ ተጽእኖ አለው። ዶክተሮች ይህን ተግባር በሚፈፅሙ ሰዎች ላይ የሚከተሉትን አደጋዎች ያስቀምጣሉ፡-📎1ኛ―የአእምሮ ባርነት (Addiction):ልክ እንደ ኮኬይን አእምሮህ ላይ የደስታ ሆርሞን (Dopamine) በውሸት እንዲረጭ ስለሚያደርግ፣ አእምሮህ ይደነዝዛል። ነገ ከትዳር አጋርህ ጋር የምታገኘው ተፈጥሯዊ ደስታ አይጣፍጥህም።🕹2ኛ―የማስታወስ ችሎታ መቀነስ እና የመርሳት ችግር፡አእምሮ ሁሌም በወሲባዊ ቅዠት ስለሚጠመድ፣ ለትምህርትና ለቂርኣት እንድሁም ለቁምነገር የሚሆን ቦታ ያጣል። ብዙ ተማሪዎችም ሆኑ ብዙ ዒልም ፈላጊዎች ትምህርታቸውን እና ዒልም መማራቸውን የጠሉት በዚህ ምክንያት ነው።😞3ኛ―የጭንቀት እና የደብርት በሽታ (Depression):ድርጊቱን ከፈጸምክ በኋላ የሚሰማህ የጥፋተኝነት ስሜት ራስን መጥላትና ባዶነት ወደ ድብርት ይወስዳል። "እኔ ርካሽ ነኝ" ብለህ እንድታስብ ያደርግሃል።👨👦4ኛ―የትዳር ህይወትን ማበላሸት፡ራስን በራስ በማርካት የለመደ ሰው፣ በትዳር ውስጥ ያለውን ትክክለኛ ግንኙነት መፈጸም ይከብደዋል (Sexual Dysfunction)። ለወንዶች የቶሎ መጨረስ ችግር (Premature Ejaculation) ዋነኛ መንስኤው ይህ መጥፎ ልማድ ነው።🎯5ኛ―የሰውነት መዛል እና የጀርባ ህመም፡የወጣትነት ጉልበትህን በከንቱ እያፈሰስክ ስለሆነ፣ ለእድገት የሚሆን ጉልበት ታጣለህ። አይንህ ይቦዝዛል፣ ጉልበትህ ይንቀጠቀጣል፣ኑርህም ይጠፋል…ከሁሉም በላይ የሚያስፈራው ግን የአኼራ ጉዳይ ነው።ውድ ወንድሜ! እስኪ ለአፍታ ቆም ብለህ አስብ!ያ በጨለማ የቆለፍከው በር ሰዎች እንዳያዩህ ነው አይደል? ግንየዓለማቱ ጌታ አላህ እየተመለከተህ እንደሆነስ ዘነጋህን?እጅህ፣ እግርህና ብልትህ ነገ በአላህ ፊት «እንዲህ አደረገብን»ብለው ሲመሰክሩብህ ምን ልትመልስ ነው? ያንተ እኩዮች ቁርኣን ሲያነቡ፣ ኢልም ሲቀስሙ፣ በትዳር ሲረጋጉ፤ አንተ ግን መጸዳጃ ቤት ውስጥ ወይም አልጋህ ላይ ከራስህ ጋር ትታገላለህ። ይህ ላንተ ክብር አይመጥንም!የወደፊት ሚስትህ ንጹህ ሆና እየጠበቀችህ፣ አንተ ግን አላህ በሐላል ላይ እንድታውለው የሰጠህን ውድ ስጦታ በቆሻሻ ቦታ እያፈሰስከው ነው። ነገ ትዳር ስትይዝ የምትሰጠው ፍቅር፣ የምትሰጠው ጉልበት ከየት ይመጣል? ጨርሰህው እኮ ነው!ሞት በዚያ ሁኔታ ውስጥ ቢመጣስ?አላህ ይጠብቀንና፣ ያንን ቆሻሻ ቪዲዮ እያየህ ወይም ያንን ሐራም እየፈጸምክ ነፍስህ ብትወጣ፣ ከአላህ ጋር እንዴት ትገናኛለህ? ወንድሜ... እህቴ... ይሄ ጉዳይ ቀልድ አይደለም። የእሳትና የጀነት ጉዳይ ነው።🔍መፍትሄው ምንድን ነው?☑ተስፋ አትቁረጥ! አላህ መሐሪ ነው። ዛሬውኑ ቆርጠህ ከተነሳህ መመለስ ትችላለህ።ወሏሂ ከዚህ ሱስ መውጣት ከባድ እንደሆነ ብታስቡም በ አላህ ከታገዛችሁና ከወሰናችሁ እጁግ በጣም ቀላል ነው።☑በንፁህ ልብ አልቅሰህ አላህን ምህረት ጠይቅ። «ጌታዬ ሆይ! ተሸነፍኩ፣ አቅም አነሰኝና እርዳኝ» በለው።☑ብቸኝነትን አጥፋ። ይህ ሱስ የሚመጣው ለብቻ ስትሆን ነው። ከሰዎች ጋር ተቀላቀል። ስልክህን መኝታ ቤት አታስገባ።☑የአይን ዚናን ተጠንቀቅ።እይታህን ስበር። በቲክቶክና በፌስቡክ የሚመጡ ስሜት ቀስቃሽ ምስሎችን አግድ (Block)። አይን የልብ መስኮት ናት።☑ጾም እና ስፖርትስራ። ነብያችን እንዳሉት ጾም ጋሻ ነው። ስፖርት ደግሞ ትርፍ ጉልበትህን በጥሩ ነገር እንድታወጣው ይረዳሃል።☑ትዳርን አስብ። አቅሙ ካለህ አግብ። ካልቻልክ እራስህን ለትዳር አዘጋጅ እንጂ በሐራም አትጨርስ።🫀ያ አላህ! በዚህ የሱስ ሰንሰለት ተጠፍረው የሚሰቃዩ ወንድም እህቶቼን አንተ ድረሰላቸው። በወንጀል የጠቆረውን ልባቸውን በምህረትህ ብርሃን አፅዳው። የዚህን ሱስ አስከፊነትና አስጠያፊነት አሳይተህ፤ ከልባቸው ጠልተው እንዲርቁትና በምትኩ የአንተን ፍቅርና የኢማንን ጣፋጭነት አላህ ይለግሳቸው። አላህ ሆይ! ወዳንተ መመለስን ለከበዳቸው ሁሉ እጃቸውን ይዘህ ወደ ብርሃን ማውጫው መንገድ ምራቸው።t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
ከረመዷን በፊት…~🕐እንደ ንፋስ በሚከንፈው የዘመን ፍጥነት ውስጥ ሆነን፣ የናፍቆት እና የራህመት ወር የሆነው ረመዳን ከደጃ...
ከረመዷን በፊት…~🕐እንደ ንፋስ በሚከንፈው የዘመን ፍጥነት ውስጥ ሆነን፣ የናፍቆት እና የራህመት ወር የሆነው ረመዳን ከደጃችን ሊደርስ እነሆ ሁለት ወራት ከሁለት ቀናት አከባቢ ብቻ ቀሩት። ነገር ግን በጊዜው እሩጫ ልክ እነዚህን ቀናት እንደ ሁለት ሳምንታት ብንቆጥራቸው ማጋነን አይሆንም።ወዳጄ ሆይ! የረመዳንን ጨረቃ መጠበቅ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ዋናው ቁምነገር ከወሩ ትሩፋት ለመቋደስ ነፍስያን አሁን ላይ ማዘጋጀት ነው። ያልታረሰ መሬት ዝናብ ቢዘንብበትም ምርቱ እንደማይሰምር ሁሉ፣ ከወዲሁ በኢባዳ ያልረጠበች ልብም ረመዳንን በአግባቡ ማስተናገድ ይከብዳታል።ስለሆነም ከዛሬ ጀምረን ራሳችንን እንፈትሽ። የቀን ተቀን ውሎአችንን በቁርኣን ድምቀት እናጅበው፤ ሌሊቱን ከእንቅልፍ በመስረቅ ለጌታችን በሚደረግ ዱዓ እና የለይል ሶላት እናድምቀው። የሶሻል ሚዲያ ጫጫታን ቀንሰን፣ ከፈጣሪያችን ጋር የምናደርገውን ቆይታ እናብዛ።ዛሬ ላይ ልባችንን ካላለዘብናት፣ ነገ ረመዳን ሲመጣ የኢባዳው ጣዕም ሊርቀን ይችላል። የረመዳን ስኬት መሰረቱ የሚጣለው ዛሬ ነው። ስለዚህ ከወዲሁ ፕሮግራማችንን አስተካክለን፣ ልባችንን አፅድተን ያን የከበረ እንግዳ እንጠብቀው።አላህ ለዚያች ለከበረች ወር በሰላም ያድርሰን!t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
❌ቁርኣንን ከዐረብኛ ቋንቋ ውጭ መፃፉ…~በአሁኑ ሰዓት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተስፋፋ የመጣ እጅግ አደገኛ አካሄድ አለ...
❌ቁርኣንን ከዐረብኛ ቋንቋ ውጭ መፃፉ…~በአሁኑ ሰዓት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተስፋፋ የመጣ እጅግ አደገኛ አካሄድ አለ። ይኸውም የአላህን ንግግር ቁርኣን የዐረብኛውን ድምፅ በአማርኛ ፊደላት ቀይሮ መፃፍ ነው (ምሳሌ፡ «ቁል ሁወላሁ...፣ «ኢዛ ጃኣ...»እያሉ መፃፍ)። ይህ ተግባር ሐራም የሆነ ተግባር ነው። ብዙ ዑለማዎችም አጥብቀው ይከለክላሉ።📖ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች ኒያችን ጥሩ ነው፣ ሰውን ለማስተማር ነው ቢሉም፤መልካም ኒያ መጥፎን ስራ ወደ ጥሩ አይቀይርም። ቁርኣን የተለየ ክብርና ጠባቂ ያለው መለኮታዊ ቃል እንጂ እንደ ግጥም በፈለግነው ፊደል የምንከትበው አይደለም።ጌታችን አላህ ቁርኣንን በዐረብኛ ቋንቋ ብቻ እና በዛው የቃላት አወቃቀር እንደመረጠው በግልፅ ተናግሯል። ቋንቋውንም ሆነ ፊደሉን መቀየር የአላህን ምርጫ መቃወም ነው።📚إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَእኛ (ፍቹን) ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው፡፡»አላህ «ዐረብኛ አድርገን አወረድነው»እያለ፤ አንተ በአማርኛ ፊደል ቀይረህ ስትፅፈው፣ አላህ ያጸደቀውን ማንነት እየቀየርክ ነው።📚በሌላ ቁርኣን አንቀፅም፦{وَلَوْ جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا أَعْجَمِيًّا لَّقَالُوا لَوْلَا فُصِّلَتْ آيَاتُهُ ۖ أَعَأْجَمِيٌّ وَعَرَبِيٌّ}«(ቁርኣኑን) በውጭ ቋንቋ (የተነበበ) ባደረግነው ኖሮ አንቀጾቹ (በዐረብኛ) ለምን አልተብራሩም ነበር? (መልክተኛው) ዐረብ (መጽሐፉ) ዐጀም (የውጭ ቋንቋ) ይሆን ነበርን? ይሉ ነበር።»ቁርኣን በሌላ ቋንቋ ንባብ (ፊደል) ቢወርድ ኖሮ ሰዎች በተቃወሙ ነበር። ዛሬ ላይ የአላህን ቃል በአማርኛ ፊደል መፃፍ ማለት የቁርኣኑን "ሙዕጂዛ" ማጥፋት ነው።🔹ሌላው እና አደገኛው ነጥብ ትርጉምን ማበላሸት ይከሰታል።ይህ ነጥብ በጣም አሳሳቢው ነው። የዐረብኛ ፊደላት ባህሪያት (መኻሪጅ) በአማርኛ ፊደላት ፈጽሞ ሊወከሉ አይችሉም። በአማርኛ ስትፅፉት የቁርኣኑ መልእክት ከምስጋና ወደ ስድብ፣ ከኢማን ወደ ኩፍር ሊቀየር ይችላል።💡ታላቁ ኢማም ማሊክ ስለ ቁርኣን አጻጻፍ ተጠይቀው እንዲህ አሉ፦"لا، إلا على الكتبة الأولى"«አይቻልም! (በሰሀቦች ዘመን) በነበረው የመጀመሪያው አጻጻፍ ቢሆን እንጂ።» ብለው መልስ ሰጥተዋል። በራሱ በዐረብኛ ቋንቋ ውስጥ እንኳን ዘመናዊ የአጻጻፍ ስልት መጠቀም ከተከለከለ ማለትም ከ "ዑስማኒ" አጻጻፍ ውጭ ሐራም ነው ከተባለ በአማርኛ ሲሆንስ እንደት ይሁን!?አላህ እውቀትንና ትክክለኛውን መረዳት ይስጠን!t.me/AbuSufiyan_Albenant.me/AbuSufiyan_Albenan
❌ቁርኣንን ከዐረብኛ ቋንቋ ውጭ መፃፉ…~በአሁኑ ሰዓት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተስፋፋ የመጣ እጅግ አደገኛ አካሄድ አለ...
❌ቁርኣንን ከዐረብኛ ቋንቋ ውጭ መፃፉ…~በአሁኑ ሰዓት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተስፋፋ የመጣ እጅግ አደገኛ አካሄድ አለ። ይኸውም የአላህን ንግግር ቁርኣን የዐረብኛውን ድምፅ በአማርኛ ፊደላት ቀይሮ መፃፍ ነው (ምሳሌ፡ «ቁል ሁወላሁ...፣ «ኢዛ ጃኣ...»እያሉ መፃፍ)። ይህ ተግባር ሐራም የሆነ ተግባር ነው። ብዙ ዑለማዎችም አጥብቀው ይከለክላሉ።📖ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች ኒያችን ጥሩ ነው፣ ሰውን ለማስተማር ነው ቢሉም፤መልካም ኒያ መጥፎን ስራ ወደ ጥሩ አይቀይርም። ቁርኣን የተለየ ክብርና ጠባቂ ያለው መለኮታዊ ቃል እንጂ እንደ ግጥም በፈለግነው ፊደል የምንከትበው አይደለም።ጌታችን አላህ ቁርኣንን በዐረብኛ ቋንቋ ብቻ እና በዛው የቃላት አወቃቀር እንደመረጠው በግልፅ ተናግሯል። ቋንቋውንም ሆነ ፊደሉን መቀየር የአላህን ምርጫ መቃወም ነው።📚إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَእኛ (ፍቹን) ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው፡፡»አላህ «ዐረብኛ አድርገን አወረድነው»እያለ፤ አንተ በአማርኛ ፊደል ቀይረህ ስትፅፈው፣ አላህ ያጸደቀውን ማንነት እየቀየርክ ነው።📚በሌላ ቁርኣን አንቀፅም፦{وَلَوْ جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا أَعْجَمِيًّا لَّقَالُوا لَوْلَا فُصِّلَتْ آيَاتُهُ ۖ أَعَأْجَمِيٌّ وَعَرَبِيٌّ}«(ቁርኣኑን) በውጭ ቋንቋ (የተነበበ) ባደረግነው ኖሮ አንቀጾቹ (በዐረብኛ) ለምን አልተብራሩም ነበር? (መልክተኛው) ዐረብ (መጽሐፉ) ዐጀም (የውጭ ቋንቋ) ይሆን ነበርን? ይሉ ነበር።»ቁርኣን በሌላ ቋንቋ ንባብ (ፊደል) ቢወርድ ኖሮ ሰዎች በተቃወሙ ነበር። ዛሬ ላይ የአላህን ቃል በአማርኛ ፊደል መፃፍ ማለት የቁርኣኑን "ሙዕጂዛ" ማጥፋት ነው።🔹ሌላው እና አደገኛው ነጥብ ትርጉምን ማበላሸት ይከሰታል።ይህ ነጥብ በጣም አሳሳቢው ነው። የዐረብኛ ፊደላት ባህሪያት (መኻሪጅ) በአማርኛ ፊደላት ፈጽሞ ሊወከሉ አይችሉም። በአማርኛ ስትፅፉት የቁርኣኑ መልእክት ከምስጋና ወደ ስድብ፣ ከኢማን ወደ ኩፍር ሊቀየር ይችላል።💡ታላቁ ኢማም ማሊክ ስለ ቁርኣን አጻጻፍ ተጠይቀው እንዲህ አሉ፦"لا، إلا على الكتبة الأولى"«አይቻልም! (በሰሀቦች ዘመን) በነበረው የመጀመሪያው አጻጻፍ ቢሆን እንጂ።» ብለው መልስ ሰጥተዋል። በራሱ በዐረብኛ ቋንቋ ውስጥ እንኳን ዘመናዊ የአጻጻፍ ስልት መጠቀም ከተከለከለ ማለትም ከ "ዑስማኒ" አጻጻፍ ውጭ ሐራም ነው ከተባለ በአማርኛ ሲሆንስ እንደት ይሁን!?አላህ እውቀትንና ትክክለኛውን መረዳት ይስጠን!t.me/AbuSufiyan_Albenant.me/AbuSufiyan_Albenan
📒―إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَٰئِكَ يُبَدِّلُ ا...
📒―إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا―«ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»🌿🌿🕯️አንዳንድ ጊዜ በህይወት ጉዞአችን ውስጥ እግሮች ይደክማሉ፣ ልቦች ይሸፍታሉ። ወንጀላችን ተራራን የሚያህል መስሎ ሲታየን፣ የፀፀት አለንጋ ህሊናችንን ሲገርፈው፣«እንዲህ አይነት በደል ፈፅሜ አላህ ይቀበለኝ ይሆን?» የሚለው የተስፋ መቁረጥ ስሜት በውስጣችን ያቃጭላል። የሰራነው ጥፋት የፈጣሪን እዝነት የሚጋርድ ይመስለናል።🌿ነገር ገን…አላህ በዚህ አንቀፅ ለተጸጸቱ ባሮቹ የገባው ቃል ኪዳን እጅግ አስደናቂ ነው። አንድ ሰው በውነት ተጸፅቶ፣ ወደ ጌታው ሲመለስና ህይወቱን በመልካም ስራ ሲያድስ፤ አላህ የሚያደርገው ነገር ልብን በደስታ ያሞቃል። «እኔ ይቅር ብዬሀለሁ»ብቻ አይልም፤ «የሰራኸውን ወንጀል ሰርዤዋለሁ» ብቻም አይልም፡፡ ከዚህም በላይ በሆነ ታላቅ ውለታ፣ «ያለፈውን መጥፎ ስራህን፣ ወደ መልካም ስራ ቀይሬልሀለሁ»ይላል።ይህ ምን አይነት እዝነት ነው? ይህ ምን አይነት ፍቅር ነው?💌አንድን ባለዕዳ፣ «እዳህን ሰርዤልሃለሁ» ከማለት አልፎ፣ «የነበረብህን እዳ ያህል በ ባንክ አካውንትህ ውስጥ ገንዘብ አስገብቼልሃለሁ» እንደማለት እኮ ነው።የሰራነው ወንጀል፣ በተውባት ሰበብ ወደ መልካም ምንዳነት ይቀየራል ማለት ነው። ያ የጨለመው የህይወት ታሪካችን፣ በብርሃን ቀለም እንደገና ይጻፋል።ስለዚህ ወዳጄ ሆይ... ወንጀልህ ቢበዛ፣ ጥፋትህ ከሰማይ ቢደርስ ተስፋ አትቁረጥ። የአላህ እዝነት ከወንጀልህ በላይ ሰፊ ነው።የሚያስፈልገው ነገር አንድ ብቻ ነው፤ የልብን በር ከፍቶ በፀፀት እንባ ታጥቦ ወደ እርሱ መመለስ።t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
ከ አላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ!~💡የወንጀልህ ብዛት እንደ ባሕር አረፋ በዝቶ ይሆናል፣ ምናልባትም የሰራሃቸው ስህተቶች እ...
ከ አላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ!~💡የወንጀልህ ብዛት እንደ ባሕር አረፋ በዝቶ ይሆናል፣ ምናልባትም የሰራሃቸው ስህተቶች እንቅልፍ ነስተውህ ይሆናል፣ ወይም ደግሞ ሰይጣን «ከእንግዲህ አንተ ወደ አላህ መመለስ አትችልም»ብሎ በጆሮህ አንሾካሹኮ ተስፋ አስቆርጦህ ይሆናል።📚ነገር ግን አላህ እንዲህ ይልሃል፦﴿قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ﴾«በነፍሶቻቸው ላይ ድንበር ላለፉት ባሮቼ (እንዲህ) በላቸው፦ ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ወንጀሎችን በሙሉ ይምራልና። እርሱ መሀሪና አዛኝ ነውና።»🔔ልብ በል! አላህ የጠራህ «ባሮቼ» ብሎ ነው። ድንበር ብታልፍም፣ ብትሳሳትም፣ ብትርቅም አሁንም ንብረትነህ የእርሱ ነው። እርሱ «ከእንግዲህ ባሪያዬ አይደለህም» አላለም። ይልቁንም በርህራሄው እቅፍ ውስጥ እንድትገባ እየጠራህ ነው።አንተ ወንጀለኛ ብትሆንም እርሱ ግን "አል-ገፋር" ነው። አንተ ድካም ቢኖርብህም እርሱ ግን "አር-ራህማን" ነው። የአላህ እዝነት ከሰማይና ከምድር የሰፋ ነው፤ ታዲያ ያንተ ወንጀል እንዴት ከእርሱ እዝነት ይበልጣል?☞ ተስፋ አትቁረጥ! የይቅርታው ደጅ አሁንም ክፍት ነው። አላህ ባሪያው በፀፀት ተመልሶ «ጌታዬ ሆይ ማረኝ»ሲለው የሚሰማው ደስታ፣ በበረሃ ግመሉን ጠፍታበት ተስፋ ቆርጦ ሳለ ድንገት አጠገቡ አግኝቷት ከሚደሰተው ሰው በላይ ነው።ዛሬውኑ ተመለስ። አንገትህን ዝቅ አድርገህ «ጌታዬ ሆይ! ተመለስኩ» በለው። እርሱ ባንተ ይቅርታ ላይ አይጨክንም። ካለፈው ጥቁር ታሪክህ ውስጥ አዲስና ብሩህ ገጽን ይከፍትልሃል።☞ወንጀል ሰርተህ ተስፋ መቁረጥህ፣ ከሰራኸው ወንጀል በላይ አላህን ያስቆጣዋል። ምክንያቱም ተስፋ መቁረጥ ማለት የአላህን ሰፊ እዝነት ማሳነስ ነው።ተነሳ! የአላህ እዝነት እየጠበቀህ ነው። ዛሬ የለውጥ ቀንህ ይሁን። ጌታህ «ተስፋአትቆርጥ» ካለህ፣ ማንም ተስፋ ሊያስቆርጥህ አይችልም!t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
~ሐቢቢ ስሜትህን ተረድቼዋለሁ። መልእክትህ ውስጥ ያለውን ህመም፣ የህሊና ጩኸት እና ከልብ የመነጨ የመላቀቅ ፍላጎት ሳነብ ...
~ሐቢቢ ስሜትህን ተረድቼዋለሁ። መልእክትህ ውስጥ ያለውን ህመም፣ የህሊና ጩኸት እና ከልብ የመነጨ የመላቀቅ ፍላጎት ሳነብ እኔም አብሬህ ተሰምቶኛል። ነገር ግን አንድ የምብስርህ ታላቅ ዜና አለኝ፤«ይህ የሚሰማህ የጥፋተኝነት ስሜት እና የድካም ስሜት፣ ልብህ አሁንም ህያው መሆኑን ትልቅ ማረጋገጫ ነው!»የሞተ ልብ አይቆጭም፣ የሞተ ልብ «ደክሞኛል» ብሎ ወደ አላህ አይጮህም። ስለዚህ ፈውስህ የሚጀምረው እዚሁ ጋር ነው።ረመዳን እየመጣ ነው። ይህ ወር የአላህ እዝነት የሚዘንብበት እንጂ፣ አንተ በሰራኸው ወንጀል ምክንያት የምትሸማቀቅበት ወር አይደለም።🔛አሁንም የምነግርህን የመፍትሄ እርምጃዎች በእርጋታ ተግብራቸው፦✔️ከራስህ ጋር ያለህን ጦርነት አቁም!«እኔ ቆሻሻ ነኝ፣ እኔ ደካማ ነኝ» እያልክ ራስህን መውቀስ አቁም። ይህ የሸይጣን ወጥመድ ነው። ሸይጣን ወንጀል እንድትሰራ ብቻ ሳይሆን፣ ከሰራህ በኋላ ተስፋ አስቆርጦህ በዛው እንድትቀጥል ነው የሚፈልገው። አንተ ደካማ አይደለህም፤ ተሸንፈህ ሳይሆን ተፈትነህ ነው። አሁን ተነስና «አላህ ሆይ! እኔ ባሪያህ ነኝ፣ እደክማለሁ፣ ነገር ግን ያንተ እዝነት ከኔ ወንጀል በላይ ነው» ብለህ አስብ።✔️በሩን ዝጋው!ይህ ችግር ድንገት አይመጣም፤ መንስኤዎች አሉት።•ስልክህ እና መኝታህን ተቆጣር።ወላሂ ይሄን ካደረግክ 50% አሸንፈሃል። ስልክህን ከመኝታ ክፍልህ አርቅ። ማታ አልጋ ላይ ሆነህ ስልክ የምትነካካ ከሆነ ለሸይጣን ቀጠሮ እየሰጠኸው ነው።• ብቻህን ፈፅሞ አትቀመጥ።ብቻህን ስትሆን አደጋው ይጨምራል። በተቻለህ መጠን ከሰዎች ጋር ተቀላቀል። ብቻህን መሆን ግድ ከሆነ ደግሞ ወዲያውኑ ዉዱእ አድርግ ወይም ቁርኣን ቅራ።•እይታህን ስበር።በማህበራዊ ሚዲያ (Tiktok, Instagram, Telegram) ስሜትህን የሚቀሰቅሱ ቻናሎች አሁኑኑ ብሎክ አድርግ። አይን የልብ መስኮት ነች፤ መስኮቱን ካልዘጋህ ቤቱ መቆሸሹ አይቀርም።✔️ስሜቱ ሲመጣብህ ወዲያውኑ አትሸነፍ። ለራስህ እንዲህ በል፡-«እሺ፣ ይህን ማድረግ ከፈለኩ አደርገዋለሁ፣ ግን ከ 5 ደቂቃ በኋላ አደርገዋለሁ በል» በዚህ 5 ደቂቃ ውስጥ ቦታ ቀይር፣ በቀዝቃዛ ውሃ ሸዋር ውሰድወይም ሁለት ረከዓ ስገድ። ስሜቱ እንደማዕበል ነው፤ ለጥቂት ደቂቃ ካለፈህ ይጠፋል። ያንን ወሳኝ ቅጽበት ማለፍ ብቻ ነው ከአንተ የሚጠበቀው።✔️ፆምን እንደ ጋሻ ተጠቀም!ረመዳን ከመግባቱ በፊት አሁን ባሉት ቀናት ሱና ፆሞችን መፆም ጀምር። ነብያችን ወጣቶችን ሲመክሩ «ለመጋባት አቅም የሌለው ይጹም፤ ፆም ለእሱ ጋሻ (መከላከያ) ነውና» ብለዋል። ፆም አካላዊ ፍላጎትህን ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ጥንካሬህንም ይገነባል።✔️ወድቀህ ታውቃለህ? እንደገና ተነስ!ይህ በጣም ወሳኝ ነው። ዛሬ ቃል ገብተህ ነገ ብትሳሳት፣ «አበቃልኝ፣ እኔ አልረባም" ብለህ ወደ ኋላ እንዳትመለስ። ሺህ ጊዜ ብትወድቅ ሺህ አንደኛ ጊዜ ተነስና ተውባ አድርግ። አላህ ተደጋጋሚ ተውባ አድራጊዎችን ይወዳል። ዋናው ቁምነገር ወድቆ አለመቅረት ነው።✅«ያ አላህ! ይህን ረመዳን አዲስ ሰው ሆኜ መቀበል እፈልጋለሁ። ይህን ቆሻሻ እተው ዘንድ፣ከዚህ ሱስ እወጣ ዘንድ አንተ እርዳኝ።» ብለህ ዱዓ አድርግ። አላህ ለአንተ አንድ ነገር ሲከለክልህ፣ የተሻለ ነገር ሊሰጥህ ፈልጎ ነው።ወንድሜ ሆይ! ይህ ነገር ላንተ ደስታ ሳይሆን ባዶነትን፣ ድካምን እና ጭንቀትን ብቻ ነው ያተረፈው። አላህ ከዚህ በላይ ክብር ይገባሃል። እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋና በሱጁድ ሆነህ አልቅስ። «ጌታዬ ሆይ አቅም አጣሁ፣ አንተ ጠብቀኝ»በል። እርዳታው ቅርብ ነው።ረመዳንን በንጹህ ልብ፣ በጠንካራ ኢማን እና በዚህ ድል ተላቀህ እንደምትቀበለው አምናለሁ። አላህ ልብህን ያፅዳው፣ ኢማንህን ያድሰው፣ ከዚህ ፈተናም ሙሉ በሙሉ ነጻ ያውጣህ። አይዞህ፣ ብቻህን አይደለህም!t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
~ሐቢቢ ስሜትህን ተረድቼዋለሁ። መልእክትህ ውስጥ ያለውን ህመም፣ የህሊና ጩኸት እና ከልብ የመነጨ የመላቀቅ ፍላጎት ሳነብ ...
~ሐቢቢ ስሜትህን ተረድቼዋለሁ። መልእክትህ ውስጥ ያለውን ህመም፣ የህሊና ጩኸት እና ከልብ የመነጨ የመላቀቅ ፍላጎት ሳነብ እኔም አብሬህ ተሰምቶኛል። ነገር ግን አንድ የምብስርህ ታላቅ ዜና አለኝ፤«ይህ የሚሰማህ የጥፋተኝነት ስሜት እና የድካም ስሜት፣ ልብህ አሁንም ህያው መሆኑን ትልቅ ማረጋገጫ ነው!»የሞተ ልብ አይቆጭም፣ የሞተ ልብ «ደክሞኛል» ብሎ ወደ አላህ አይጮህም። ስለዚህ ፈውስህ የሚጀምረው እዚሁ ጋር ነው።ረመዳን እየመጣ ነው። ይህ ወር የአላህ እዝነት የሚዘንብበት እንጂ፣ አንተ በሰራኸው ወንጀል ምክንያት የምትሸማቀቅበት ወር አይደለም።🔛አሁንም የምነግርህን የመፍትሄ እርምጃዎች በእርጋታ ተግብራቸው፦✔️ከራስህ ጋር ያለህን ጦርነት አቁም!«እኔ ቆሻሻ ነኝ፣ እኔ ደካማ ነኝ» እያልክ ራስህን መውቀስ አቁም። ይህ የሸይጣን ወጥመድ ነው። ሸይጣን ወንጀል እንድትሰራ ብቻ ሳይሆን፣ ከሰራህ በኋላ ተስፋ አስቆርጦህ በዛው እንድትቀጥል ነው የሚፈልገው። አንተ ደካማ አይደለህም፤ ተሸንፈህ ሳይሆን ተፈትነህ ነው። አሁን ተነስና «አላህ ሆይ! እኔ ባሪያህ ነኝ፣ እደክማለሁ፣ ነገር ግን ያንተ እዝነት ከኔ ወንጀል በላይ ነው» ብለህ አስብ።✔️በሩን ዝጋው!ይህ ችግር ድንገት አይመጣም፤ መንስኤዎች አሉት።•ስልክህ እና መኝታህን ተቆጣር።ወላሂ ይሄን ካደረግክ 50% አሸንፈሃል። ስልክህን ከመኝታ ክፍልህ አርቅ። ማታ አልጋ ላይ ሆነህ ስልክ የምትነካካ ከሆነ ለሸይጣን ቀጠሮ እየሰጠኸው ነው።• ብቻህን ፈፅሞ አትቀመጥ።ብቻህን ስትሆን አደጋው ይጨምራል። በተቻለህ መጠን ከሰዎች ጋር ተቀላቀል። ብቻህን መሆን ግድ ከሆነ ደግሞ ወዲያውኑ ዉዱእ አድርግ ወይም ቁርኣን ቅራ።•እይታህን ስበር።በማህበራዊ ሚዲያ (Tiktok, Instagram, Telegram) ስሜትህን የሚቀሰቅሱ ቻናሎች አሁኑኑ ብሎክ አድርግ። አይን የልብ መስኮት ነች፤ መስኮቱን ካልዘጋህ ቤቱ መቆሸሹ አይቀርም።✔️ስሜቱ ሲመጣብህ ወዲያውኑ አትሸነፍ። ለራስህ እንዲህ በል፡-«እሺ፣ ይህን ማድረግ ከፈለኩ አደርገዋለሁ፣ ግን ከ 5 ደቂቃ በኋላ አደርገዋለሁ በል» በዚህ 5 ደቂቃ ውስጥ ቦታ ቀይር፣ በቀዝቃዛ ውሃ ሸዋር ውሰድወይም ሁለት ረከዓ ስገድ። ስሜቱ እንደማዕበል ነው፤ ለጥቂት ደቂቃ ካለፈህ ይጠፋል። ያንን ወሳኝ ቅጽበት ማለፍ ብቻ ነው ከአንተ የሚጠበቀው።✔️ፆምን እንደ ጋሻ ተጠቀም!ረመዳን ከመግባቱ በፊት አሁን ባሉት ቀናት ሱና ፆሞችን መፆም ጀምር። ነብያችን ወጣቶችን ሲመክሩ «ለመጋባት አቅም የሌለው ይጹም፤ ፆም ለእሱ ጋሻ (መከላከያ) ነውና» ብለዋል። ፆም አካላዊ ፍላጎትህን ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ጥንካሬህንም ይገነባል።✔️ወድቀህ ታውቃለህ? እንደገና ተነስ!ይህ በጣም ወሳኝ ነው። ዛሬ ቃል ገብተህ ነገ ብትሳሳት፣ «አበቃልኝ፣ እኔ አልረባም" ብለህ ወደ ኋላ እንዳትመለስ። ሺህ ጊዜ ብትወድቅ ሺህ አንደኛ ጊዜ ተነስና ተውባ አድርግ። አላህ ተደጋጋሚ ተውባ አድራጊዎችን ይወዳል። ዋናው ቁምነገር ወድቆ አለመቅረት ነው።✅«ያ አላህ! ይህን ረመዳን አዲስ ሰው ሆኜ መቀበል እፈልጋለሁ። ይህን ቆሻሻ እተው ዘንድ፣ከዚህ ሱስ እወጣ ዘንድ አንተ እርዳኝ።» ብለህ ዱዓ አድርግ። አላህ ለአንተ አንድ ነገር ሲከለክልህ፣ የተሻለ ነገር ሊሰጥህ ፈልጎ ነው።ወንድሜ ሆይ! ይህ ነገር ላንተ ደስታ ሳይሆን ባዶነትን፣ ድካምን እና ጭንቀትን ብቻ ነው ያተረፈው። አላህ ከዚህ በላይ ክብር ይገባሃል። እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋና በሱጁድ ሆነህ አልቅስ። «ጌታዬ ሆይ አቅም አጣሁ፣ አንተ ጠብቀኝ»በል። እርዳታው ቅርብ ነው።ረመዳንን በንጹህ ልብ፣ በጠንካራ ኢማን እና በዚህ ድል ተላቀህ እንደምትቀበለው አምናለሁ። አላህ ልብህን ያፅዳው፣ ኢማንህን ያድሰው፣ ከዚህ ፈተናም ሙሉ በሙሉ ነጻ ያውጣህ። አይዞህ፣ ብቻህን አይደለህም!t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
🎓አልሐምዱሊላህ!~አልሐምዱሊላህ! ምስጋና ሁሉ ይህንን ኪታብ አስጀምሮ በሰላም ላስፈጸመን ጌታ ይገባው። ጅማሬው ያማረ ፍጻሜ...
🎓አልሐምዱሊላህ!~አልሐምዱሊላህ! ምስጋና ሁሉ ይህንን ኪታብ አስጀምሮ በሰላም ላስፈጸመን ጌታ ይገባው። ጅማሬው ያማረ ፍጻሜውም የሰመረ እንዲሆን የረዳን እሱ ነውና ምስጋና ሁሉ ለርሱ ይሁን።ይህ ኪታብ ለህይወታችን መስተካከል፣ ለልባችን መጠገን፣ እንዲሁም ወደ አላህ ለመቅረባችን ሰበብ እንዲሆንልን እመኛለሁ። የቀራነው እውቀት ከምላስ አልፎ ልብ ውስጥ የሚዘልቅ፣ በተግባር ተለውጠን የምንታይበትና አላህ ዘንድ በኢኽላስ የምንመዘንበት ያድርግልን።እኔም ገና ጧሊበል ዒልም እንኳ ደረጃ ያልደረስኩኝ አንድ ደካማ ወንድማችሁ ነኝና፤ይህን ኪታብ ሳቀራ የተሳሳትኩት፣ ያዛባሁት ወይም ያበላሸሁት ነገር ካለ «ማስተካከልን እንጂ ማበላሸትን አልሻምና» አላህ ይቅር እንዲለኝ እማጸነዋለሁ። እናንተም በሰማችሁት እውነት ተጠቃሚ፤ በሠራሁት ስህተት ደግሞ ከራሴና ከሸይጣን መሆኑን አውቃችሁ ይቅር እንድትሉኝ እጠይቃለሁ።በሉ እንግዲህ ከፊታችን ያለው ረመዷን ነውና... በዱዓችሁ አትርሱኝ።ወቢላሂ ተውፊቅ!✒️ወንድማችሁ አቡ ሱፍያን
አደራህን! ይህን ክቡር እንግዳ በቆሻሻ ተግባር እንዳታስቀይመው!~ውድ ወንድሜ! ረመዳን ማለት አመት ጠብቆ የሚመጣ የአላህ ...
አደራህን! ይህን ክቡር እንግዳ በቆሻሻ ተግባር እንዳታስቀይመው!~ውድ ወንድሜ! ረመዳን ማለት አመት ጠብቆ የሚመጣ የአላህ ስጦታ ነው፤ የራህመት ዝናብ የሚወርድበት፣ የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት ልዩ ወር። ታዲያ ይህን ክቡር እንግዳ እንዴት በቆሻሻ ተግባር ትቀበለዋለህ? እንዴትስ በውስጡ ቆሻሻ ተግባር ትፈፅማለህ?✔️አላህ ላንተ ሲል በረመዳን ቀን የፈቀደልህን፣ሀላል የሆነውን ውሃና ምግብ «ተውልኝ» ብሎ አዘዘህ። አንተም «እሺ ጌታዬ» ብለህ ዋልክ። ነገር ግን ፀሀዩ ገና ሳይጠልቅ፤ ጉሮሮህ በውሃ ጥም እየደረቀ፣ ሆድህ በረሃብ እየተላወሰ... አላህ «ተወው» ያለህን ምግብ ትተህ፤ አላህ «አትቅርበው» ያለህን አስጠያፊ ወንጀል ትፈፅማለህ?ይህ እንዴት ያለ ውርደት ነው? በአንድ በኩል «ጌታዬ ሆይ ፆመኛ ነኝ»እያሉ፤ በሌላ በኩል የረመዳንን ክብር በመጋፋት፣ መላኢካዎች በሚያዩበት ሰዓት ያን ታላቅ ወንጀል መፈፀም እንዴት የሞራል ልዕልና ይኖረዋል?✔ይህ ተግባር ፆምን እንደሚያበላሽ፣ የዚያን ቀን ልፋት ወደ ዜሮ እንደሚያወርደውና ቀዷ እንደሚያስወጅብ ዑለማዎች ይናገራሉ። ግን ከዛም በላይ የሚያስፈራው...የረመዳንን ቀን ክብር መድፈርህነው።አንድ ሰው ንጉስ ፊት ቆሞ ወንጀል ቢሰራና ሜዳ ላይ ወንጀል ቢሰራ እኩል አይደለም። በረመዳን የምትሰራው ወንጀል አላህ ዘንድ እጅግ ያስቆጣል። ፆም ማለት ስሜትን መግራት እንጂ፤ በረሃብ ተቀጥቶ በስሜት መሸነፍ ማለት አይደለም።✔️ረመዳን ሸይጧን የሚታሰርበት ወር ነው። ታዲያ በዚህ ወር ይህን አስቀያሚ ሱስ ከፈፀምክ፤ ጠላትህ ሸይጧን ሳይሆን የራስህ ስሜት፣ነፍስያህ መሆኗን አወቅክ ማለት ነው። ይህ ወር እኮ ነፍስያን የምትገራበት ወር እንጂ፤ እጅ ሰጥተህ የምትዋረድበት ወር አይደለም።✔️ውድ ወንድሜ! ውሃን መተው የቻለ ማንነትህ፤ እንዴት ይህን ተግባር መተው ያቅተዋል? ለአላህ ብለህ ለሰዓታት ከምግብ ከተቆጠብክ፤ ለአላህ ብለህ ለደቂቃዎች ከሚቆይ የውሸት እርካታ መቆጠብ አያቅትህም።እስቲ አስበው... ልክ ይህን አስቀያሚ ተግባር ፈፅመህ፣ ፆምህን አበላሽተህ፣ ገላህ ሳይታጠብ (ጀናባ ላይ ሆነህ) የሞት መላአክ ቢመጣስ? አላህ ዘንድ በምን ፊት ትቀርባለህ? «ጌታዬ ሆይ ሰዎች ሲፆሙ እኔ ስሜቴን በገዛ እጄ ሳረካ ነበር የመጣሁት» ልትል ነው?ይህ ረመዳን ላንተ የመጣው ከዚህ ሱስ እንድትላቀቅ ነው። ይህን ወር ካልተጠቀምክበት መቼ ልትለወጥ ነው?ወንድሜ. አሁን ባለሁበት ቁርጠኛ ሁን። «በቃኝ!»በል።✅ጌታህን «ደካማ ባሪያህ ነኝና አግዘኝ»ብለህ ለምነው።ከዚህ ሱስ አላህ እንዳወጣህ በዱዓ ላይ በርታ።✅ብቸኝነትን ሽሽ፤ ስልክህን ከእጅህ አርቅ። እንድሁም የምትበላውን ምግብ ምረጥ።ቴምር እና መሰል ጣፋጭ ምግቦችን…ስሜት የሚያበረታቱ በልኩ ተመገብ። በዚህ ወር ካልተወጣኸው በሌላ ጊዜ ይከብድሃልና መሞከርህን ቀጥል!ያረብ በዚህ ሱስ የተለከፈን ሁሉ፤ ረመዳንን እራሳቸውን የሚያሸንፉበት የድል ወር አድርግላቸው።ይህ ረመዷን ከዚህ ሱስ የመውጫቸው ዕድል አድርግላቸው!➡️⇝✈️t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
🌷የተከበርሽ እህቴ! ሐቂቃ ይህን ጥያቄሽን ሳነብ መጀመሪያ የተሰማኝ ደስታ ነው። አዎ! ደስታ! ምክንያቱም «ኢማኔ አልጨመረ...
🌷የተከበርሽ እህቴ! ሐቂቃ ይህን ጥያቄሽን ሳነብ መጀመሪያ የተሰማኝ ደስታ ነው። አዎ! ደስታ! ምክንያቱም «ኢማኔ አልጨመረም፣ ቀልቤ አልለሰለሰም»ብለሽ መጨነቅሽ እና መፍትሄ መፈለግሽ ራሱ በውስጥሽ ህያው የሆነ፣ አላህን ፈላጊና ንፁህ ልብ እንዳለሽ ትልቅ ማሳያ ነው።🫀የሞተ ልብ እኮ ህመሙ አይሰማውም፤ የደነደነ ልብም ስለ ድንዛዜው አይጨነቅም። ስለዚህ ይህ ስሜትሽ የኢማንሽ አንዱ አካል ነውና በቅድሚያ አላህን አመስግኚ።እህቴ፤ ቁርኣን እየቀራሽ፣ ተራዊህ እየሰገድሽ ነገር ግን ለውጥ ካልታየሽ፣ ችግሩ ያለው ከድርጊቱ ብዛት ላይ ሳይሆን «ከድርጊቱ ጥራት»ላይ ነው። ስለዚህ በቀሪዎቹ የረመዷን ቀናት ይህን የደረቀ ስሜት ለማርጠብ ለ እኔም ላንችም ይጠቅማሉ የምላቸው፦1⃣ከብዛት ይልቅ ጥራት ላይ አተኩሪ!ቁርኣንን በቶሎ ለማኸተም ብቻ ብለሽ አትሩጪ። ልብ የሚለሰልሰው በገፆች ብዛት ሳይሆን በማስተንተን ነው። አንድ ጁዝ ፈጥነሽ ከምታነቢ፣ ትርጉሙን እያሰብሽ፣ መልእክቱ ለኔ ነው የተባለው እያልሽ አንድ ገፅ ብታነቢ ለቀልብሽ ፈውስ ነው። አላህ የጀነትን ነገር ሲያነሳ ጀነትን ተመኚ፣ የጀሀነምን ሲያነሳ በአላህ ተጠበቂ። ቁርኣኑን የህይወትሽ መስተዋት አድርጊው።2⃣የሱጁድሽን ጊዜ አስረዝሚ!ተራዊህ ስትሰግጂ ከኢማሙ ጋር ከሰገድሽ በኋላ፣ ለብቻሽ በሌሊት ተነስተሽ ሁለት ረከዓ ስገጂ። በዛች ሰላት ላይ ሱጁድሽን እጅግ በጣም አስረዝሚው። ሱጁድ ውስጥ ሆነሽ ማንም ሳያይሽ፣ በጌታሽ ፊት ውርደትሽን አሳይተሽ አልቅሺ። እምባ ካልመጣልሽም ለማልቀስ ሞክሪ (ተባኪ)።«ያ ረብ! አካሌ አንተ ፊት ወድቋል፣ ነገር ግን ልቤ ደንድኖብኛል። ድንጋይ የሆነውን ልቤን በራህመትህ አርጥብልኝ፣ አንተን የማፍቀርን ጣዕም አቅምሰኝ» ብለሽ በራስሽ ቋንቋ አውሪው። አላህ የተሰበረን ልብ መጠገን ይወዳል።3⃣የሌሎችን ልብ በማስደሰት የራስሽን ልብ አልስልሺ!ነብዩ አንድ ልቡ እንደደነደነበት ላማረረ ሰው የሰጡት ምክር «የየቲምን ራስ ዳብስ፣ ሚስኪንን መግብ» የሚል ነበር። በዚህ ረመዷን አቅምሽ በፈቀደው ፆመኛን አስፈጥሪ፣ ለተቸገረ ሰደቃ ስጪ፣ ወላጆችሽን ወይም ጎረቤትሽን በፈገግታ አናግሪ። ከሰዎች ጋር የምታደርጊው መልካም ግንኙነት እና የነሱን ዱዓ ማግኘት ቀጥታ የራስሽን ልብ ያለሰልሰዋል።4⃣ዚክር እና እስቲግፋር አብዢ!ልብ በዱንያ ሀሳብ፣ በሀሜት ወይም ባልታሰቡ ጥቃቅን ወንጀሎች ምክንያት ሸረሪት እንደሚያደራበት ቤት ይዝጋል። የዚህ ዝገት ማፅጃው ደግሞእስቲግፋር(አስተግፊሩላህ) ማለት ነው። በተለይ «ያ ሙቀሊበል ቁሉብ! ሰቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒክ» (አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታ ሆይ! ልቤን በሀይማኖትህ ላይ አፅናልኝ) የሚለውን የነብዩን (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዱዓ ከምላስሽ አትለይ።5⃣ከ ስልክሽ ጋር ያለሽን ግንኙነት ቀንሺ!ብዙ ጊዜ ልባችንን የሚያደርቀው እና የኢባዳ ጣዕም የሚያሳጣን፣ ከቁርኣን ይልቅ ለሶሻል ሚዲያ (ቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ዩትዩብ ወዘተ) የምንሰጠው ጊዜ ነው። ስክሪን ላይ ብዙ ሰዓት ማሳለፍ የቀልብን ብርሀን ያጠፋል። ቢያንስ በዚህ ረመዷን ከስልክሽ ራቅ ብለሽ ከራስሽ እና ከጌታሽ ጋር ብቻ የምትሆኚበት (ኸልዋ) ጊዜ ይኑርሽ።🗓እህቴ... ገና በ6ኛው ቀን ላይ ነን። ጊዜው. አላለፈም፤ ይልቁንም ትልቁና በረካው የሞላበት ጊዜ ገና ከፊታችን ነው። በ6ኛው ቀን ይህን ስሜት ማስተዋልሽ ራሱ ትልቅ የንቃት እድል ነውና ቀሪዎቹን ቀናት በተሻለ ሁኔታ እንድትጠቀሚባቸው ያግዝሻል።🫴ውድ እህቴ! ልብ የሚለሰልሰው በአንድ ጀንበር ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን ከላይ የጠቀስናቸውን ተግባራት ላይ በፅናት ከቀጠልሽ አላህ የልብሽን መድረቅ ወደ ለምለም የኢማን እርጥበት ይቀይርልሻል።አላህ በዚህ በተባረከ ወር ልብሽን በኑር ያበራልሽ፣ የኢማንን ጣዕም ያቅምስሽ፣ ያሰብሽውንም የለውጥ ደረጃ ያጎናፅፍሽ።ቀሪው የረመዷን ጊዜ ለእኔም ላንቺም የእውነተኛ ለውጥ፣ የምህረት እና ከእሳት ነፃ የምንወጣበት ያድርግልን!t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
📢ታላቅ የቁርኣን ቲላዋ ውድድር!📖አጅርንም ሽልማትንም የሚያስገኝ አጓጊ የቁርኣን ቲላዋ ውድድር ይዘንላችሁ ቀርበናል!📒የውድ...
📢ታላቅ የቁርኣን ቲላዋ ውድድር!📖አጅርንም ሽልማትንም የሚያስገኝ አጓጊ የቁርኣን ቲላዋ ውድድር ይዘንላችሁ ቀርበናል!📒የውድድሩ ህግና ደንብ፦1️⃣አላላክ፦ተወዳዳሪዎች የቁርኣን አቀራራችሁን በድምፅ (Voice) በመቅዳት ከሙሉ ስማችሁ ጋር በውስጥ መስመር ትልኩልናላችሁ።2️⃣የመጀመሪያ ማጣሪያ፦ከተላኩት ድምፆች መሀል ቻናል ላይ የምንለቀው ለውድድር ብቁ ናቸው ብለን ያመንባቸውን የተመረጡ ቅጂዎች ብቻ ይሆናል።3️⃣የአድማጭ ድምፅ (Like)፦ቻናል ላይ ከተለቀቁት ተወዳዳሪዎች ውስጥ በአድማጭ ብዙ 'Like' (👍) ያገኙ10 ተወዳዳሪዎችብቻ ተለይተው ወደ ፍፃሜው ዙር ያልፋሉ።4️⃣የመጨረሻ ዳኝነት፦10ሩ ከፍተኛ ድምፅ ያገኙ ተወዳዳሪዎች በኡስታዞች የ"ተጅዊድ" እና አጠቃላይ የአቀራር ህግጋት መመዘኛ ታይተው ከ1ኛ እስከ 3ኛ የሚወጡት ይለያሉ።❌ማሳሰቢያ!የአድማጮች ላይክ (Like) መመዘኛ ያደረግነው ተወዳዳሪዎች ስለሚበዙ አቅልለን 10 ምርጦችን ለማውጣት እንጂዋናው የውድድሩ መመዘኛ የተጅዊድ ህግነው። ስለዚህ ብዙ 'Like' አግኝቶ ነገር ግን በኡስታዞች ምዘና ተጅዊዱ ውድቅ የሆነ ተወዳዳሪ አሸናፊ መሆን አይችልም!🏆በኡስታዞች ተመዝነው ከ1ኛ እስከ 3ኛለሚወጡ ምርጥ ተወዳዳሪዎች ሽልማት አዘጋጅተናል!🎁🕑የመላኪያጊዜ፡ከ አሁን ሰዓት እስከ ዕሮብ 11 ሰዓት ድረስ ይሆናል።😎t.me/Sle_qelbachn1
⏰የሰዓት ማሻሻያ ማስታወቂያ!📖ውድ ተወዳዳሪዎች፤ የቲላዋ መቀበያ ሰዓታችን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ መሆኑን አሳውቀን የ...
⏰የሰዓት ማሻሻያ ማስታወቂያ!📖ውድ ተወዳዳሪዎች፤ የቲላዋ መቀበያ ሰዓታችን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ መሆኑን አሳውቀን የነበረ ቢሆንም፣ ካሰብነው በላይ እጅግ በርካታ (ከ240 በላይ) ተወዳዳሪዎች በመመዝገባቸው ሰዓቱን ወደ 6፡00 ሰዓት ዝቅ አድርገነዋል።ይህን ማድረግ ያስፈለገን ኡስታዞቻችን ሁሉንም ቲላዋዎች አዳምጠው ለማጣራትና ዳኝነት ለመስጠት ጊዜ ስለሚያንሳቸው ነው። በመሆኑም ከዚህ ሰዓት በኋላ ተጨማሪ ቲላዋ የማንቀበል መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን። ላሳያችሁት ከፍተኛ ፍላጎት አላህ ይመንዳችሁ! (ጀዛኩሙላሁ ኸይረን!)
ትኩረት!~✅ብዙዎች መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ የተለቀቁትን ሪከርዶች ብቻ አዳምጠው ላይክ ሲሰጡ አስተውለናል። ነገር ግን በ...
ትኩረት!~✅ብዙዎች መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ የተለቀቁትን ሪከርዶች ብቻ አዳምጠው ላይክ ሲሰጡ አስተውለናል። ነገር ግን በመካከል የተለቀቁ ያላዳመጣችኋቸው ውብ ቲላዋዎች ስላሉ፤ እባካችሁ ላይክ ከመስጠታችሁ በፊት ሁሉንም ተወዳዳሪዎች በጥሞና አዳምጡ።✅እንድሁም ቀደም ሲል ላይክ ማድረግ የሚቻለው ሪከርዱ በተለቀቀ በ15 ደቂቃ ውስጥ ብቻ ነበር። አሁን ግን ዘግይተው የሚገቡ አድማጮችን ከግምት በማስገባት፣ እያንዳንዱ ቲላዋ ከተለቀቀበት ሰዓት ጀምሮ የድምፅ መስጫ ጊዜውወደ 24 ሰዓትተራዝሟል!
🤲ያ ጀባር...ያለፈውን ቁስላችሁን የሚያሽር፣ የትላንቱን ህመማችሁን የሚያስረሳ፣ ለዲናችሁም ለዱንያችሁም ብርሃን የሚሆን አ...
🤲ያ ጀባር...ያለፈውን ቁስላችሁን የሚያሽር፣ የትላንቱን ህመማችሁን የሚያስረሳ፣ ለዲናችሁም ለዱንያችሁም ብርሃን የሚሆን አይን ማረፊያ የትዳር አጋር ይወፍቃችሁ። "ለካስ ያጣሁት ለዚህኛው ፀጋ ነው!" ብላችሁ በደስታ እስክታለቅሱ ድረስ፣ ከምትመኙት በላይ አድርጎ ጌታዬ ይካሳችሁ።✅ስለ ቀልባችን
የልብ ህክምና...~🗓ቀናቶች እንደ ዐይን እርግብግብ እያሉ ሮጠው፣ ሌሊቶች ተፈራርቀው እነሆ የረመዳን የመጨረሻዎቹ አስር ወ...
የልብ ህክምና...~🗓ቀናቶች እንደ ዐይን እርግብግብ እያሉ ሮጠው፣ ሌሊቶች ተፈራርቀው እነሆ የረመዳን የመጨረሻዎቹ አስር ወርቃማ ቀናት ደጃፋችን ላይ ቆመዋል። ዱንያ በግርግሯ፣ በጫጫታዋና ማለቂያ የሌለው ሩጫዋ አድክማናለች። ነፍሳችን በምድራዊ ሀሳብ ታውካለች፤ ልባችንም በሀጢያት ደብዝዟል። ታዲያ ለዚህች የዛለች ነፍስና ለቆሰለ ልብ ከጌታዋ እቅፍ የተሻለ ምን ማረፊያ አላት?እነሆ የነብዩን (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱና ህያው ለማድረግና ከጌታው ጋር መገናኘትን ለናፈቀ ልብ፣ ኢዕቲካፍ መግባት ለሚፈልጉ ወንድምና እህቶችዛሬ ሰኞ ከዐሱር ሶላት በኋላወደ ተመረጡት የአላህ ቤቶች መግቢያችሁ ነው።ኢዕቲካፍ ማለት ዝም ብሎ መስጂድ ውስጥ መተኛት፣ ወይም ከሰዎች ተነጥሎ ጊዜ ማሳለፍ ብቻ አይደለም። የኢዕቲካፍ ዋነኛ አላማ"ቀልብን ማስተካከል"ነው። በዱንያ ሩጫ የተበታተነውን ልብ ሰብስቦ ወደ አላህ መመለስ ነው። ከአላህ ጋር ብቻ መገለል ማለት የነፍስን ጥማት የሚያረካ፣ የልብን ስብራት የሚጠግን ልዩ ፀጋ ነው።🔚ስልካችንን፣ ስራችንን፣ ማህበራዊ ሚዲያውንና የዱንያን ሀሳብ ሁሉ ከጀርባችን ትተን፤ "ጌታዬ ሆይ! ሁሉንም ትቼ፣ ከሁሉ ሸሽቼ ወዳንተ መጥቻለሁ፤ ልቤን አፅዳልኝ፣ ነፍሴን አሳምርልኝ" የምንልበት የፍቅር ቀጠሮ ነው። ጫጫታ በበዛበት በዚህ አለም ውስጥ፣ የውስጣችንን የአላህ ጥሪ መስማት የምንችለው በዝምታና ከጌታ ጋር በሚደረግ ኸልዋ ውስጥ ብቻ ነው።በነዚህ አስር ቀናት ውስጥ ሌሊቱ ልዩ ጣዕም አለው። ሰዎች ሁሉ በእንቅልፍ ሲያሸልቡ፣ አንተ ግን ለጌታህ በሌሊት ሶላት ትቆማለህ። በሱጁድህ ላይ ግንባርህን መሬት አስደግፈህ፣ እንባህን ታፈሳለህ። ያሳለፍከውን የሀጢያት ዘመን እያሰብክ፣ ድካምህንና ብሶትህን ሁሉ ለሰሚው ጌታ ታዋያለህ።ይህች ዱንያ አጭር ናት። የሰው ልጅ ልብ ሁልጊዜ ወደ ምድር እያየ ከሰማዩ ጌታ ርቋል። ኢዕቲካፍ ግን ልባችንን ክንፍ አውጥቶ ወደ ሰማይ እንዲበር፣ ከፈጣሪው ጋር እንዲገናኝ ያደርገዋል።⚠️ምናልባትም... ይህ የመጨረሻው ረመዳናችን ሊሆን ይችላል። ቀጣዩን አመት ማን ያውቃል? ስለዚህ አሁኑኑ ተነሳ! ዛሬ ሰኞ ከዐሱር በኋላ ልብህን ሰብስበህ፣ ኒያህን አጥርተህ ወደ አላህ ቤት ግባ። አላህ በኢዕቲካፍህ ቀልብህን ያስተካክልልህ፣ ሀሳብህን ይሰብስብልህ። ሌይለተል ቀድርን አግኝተው፣ ወንጀላቸው ተማሮ፣ ከእሳት ነፃ ከሚወጡት ምርጥ ባሮቹ ያድርገን።➡️t.me/Sle_qelbachn1➡️t.me/Sle_qelbachn1
ሸይኽ ሱለይማንን ያስለቀሳቸው የ አንድት እህት ጥያቄ!አንዲት ጠያቂ እንዲህ ትላለች፡-«በተለያዩ የዝሙት አይነቶች እና በታ...
ሸይኽ ሱለይማንን ያስለቀሳቸው የ አንድት እህት ጥያቄ!አንዲት ጠያቂ እንዲህ ትላለች፡-«በተለያዩ የዝሙት አይነቶች እና በታላላቅ ወንጀሎች ውስጥ ወድቃ እንደነበር፣ እንዲሁም ብዙ አስቀያሚ ኃጢአቶችን እንደፈጸመች ጠቅሳለች። ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን ወደ አላህ ተውበት አድርጋ ባጠፋችው ጥፋት ክፉኛ ተጸጽታ አሁን ትዳር መመስረት ትፈልጋለች።ታዲያ አሁን ምን ማድረግና ምን ማለት አለባት? 'ከዚህ በፊት የሰራሁትን ወንጀል (ለሚያገባኝ) ባሌ ሳልነግረው ባገባ ጋብቻዬ ትክክል ይሆናልን?' ትላለች።የሸይኽ ሱለይማን አር-ሩሐይሊ መልስ፡«አላህ ለእኛም ለእሷም እንዲምረን፣ ተውበታችንንም እንዲቀበለን፣ የሁላችንንም ወንጀል እንዲምረን እለምነዋለሁ።ወደ መልሱ ስንመጣ፡አንደኛ፡ለዚህች እህት እንኳን ደስ አለሽ እንላታለን። ተውበት በማድረጓ ልትደሰት ይገባል። ተውበት ማድረግና ወደ አላህ መመለስ ምንኛ ያማረ ነው!ሁለተኛ፡ከዚህ ቀደም የሰራቻቸውን አስቀያሚ ወንጀሎች ለማንም ሰው መናገር አይጠበቅባትም፤ ሊያገባት ለሚመጣው ሰውም ቢሆን መናገር የለባትም።ነገር ግን (በማህበረሰቡ ዘንድ) ድንግል እንደሆነች የሚታሰብ ከሆነ፣ ለሚያገባት ሰው 'ድንግል እንዳልሆነች' ብቻ ልትነግረው ይገባል። ይህን መናገሯ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ምክንያቱን እንዴት ድንግልናዋን እንዳጣች መናገር አይጠበቅባትም።ድንግል እንዳልሆነች ብቻ ትንገረው እንጂ በምን ምክንያት እንደሆነ አትግለጽለት።ከዚህ ውጪ ግን ከተውበት በፊት በወንጀል ህይወት ውስጥ እያለች የሰራችውን ማንኛውንም ነገር ለማንም መናገር አያስፈልጋትም አይጠበቅባትም።»t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
⚠️ዛሬ ማታ...⏰ከረመዳን ሌሊቶች ሁሉ 'ለይለተል ቀድር' ትሆናለች ተብላ በጉጉት የምትጠበቀውና ትልቁን ግምት የምትወስደው...
⚠️ዛሬ ማታ...⏰ከረመዳን ሌሊቶች ሁሉ 'ለይለተል ቀድር' ትሆናለች ተብላ በጉጉት የምትጠበቀውና ትልቁን ግምት የምትወስደው 27ኛዋ ሌሊት ላይ ደርሰናል።ወንድም እህቶቼ… ዛሬ ማታ መተኛት በፍጹም አይታሰብም! አቅም ለማሰባሰብና ማረፍ ለምትፈልጉ አሁኑኑ ትንሽ አረፍ በሉ እንጂ፣ ሌሊቱን በሙሉ ንቁ ሆነን ልንጠብቀው ይገባል።ይህችን ታላቅ ሌሊት በከንቱ እንዳናባክናት፤ በሶላት እንቁም፣ ቁርኣንን እናንብብ፣ አንደበታችን በዚክር ይርጠብ። የሺህ ወር በረካን ላለማጣት አሁኑኑ ራሳችንን እናዘጋጅ!t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
🕐በቃ ልትሄድ ነው...አልረሳሁም እኔ፣ አዎ! ትዝ ይለኛል፤አምና ስትሄድብኝ እምባ እምባ ብሎኛል።እንደምትሄድ ሳስብ ሰላሜን...
🕐በቃ ልትሄድ ነው...አልረሳሁም እኔ፣ አዎ! ትዝ ይለኛል፤አምና ስትሄድብኝ እምባ እምባ ብሎኛል።እንደምትሄድ ሳስብ ሰላሜን ነስቶኛል፤በአላህ ውሳኔ ተሰናብተኸኛል።አዎ! የማይሄድ የለም፣ ቀኑ ነጎደና፤ከአስራ አንድ ወር በኋላ መጣህ እንደገና።መምጫህ ሲቃረብ የደስታዬን ብዛት፤መናገር አልችልም፣ የለኝምም ቃላት።ያ ሸህረ ረመዷን!!ዳግም አገኘሁህ ሳልገባ ከቀብር፤በህይወት ቆይቼ ሳልወጣ ከምድር።ይመስገን ጌታዬ ላቅ ያለ ምስጋናን፤ስላደረሰኝ ለሸህሩ ረመዷን።በደስታ ነበረ እኔ የተቀበልኩህ፤ናፍቀኸኝ ነበረ፣ እንኳን አገኘሁህ።ደስተኛ ሆኛለሁ ከምነግርህ በላይ፤ሁኔታዬ ሲታይ አይመስልም ምንለያይ።ግና ይኸው በቃ ልትጓዝ ነው፤ከልቤ ሳልጠግብ "ቻው" እያልከኝ ነው።እንግዲህ ደህና ሁን፣ በቃ ልትሄድ ነው?!ብሶት ብሶት አለኝ፣ አንጀቴን በላኸው።ከደጃፍ ቆመሃል ልትሰናበተኝ፤አንተን መሸኘት ግን እጅጉን ከበደኝ።በቃ ልትሄድ ነው? እንግዳም አልነበርክ?!በጣም ነው ምወድህ፣ ትናፍቀኛለህ!!እጄን ከፍ አድርጌ ለመንኩህ ያ አላህ፤ዳግም አገናኘኝ ከታላቁ ወርህ።እኔስ አልቻልኩም፣ ሀቂቃ ከበደኝ፤እንግዲህ ጌታዬ ብርታቱን ለግሰኝ።እያልኩኝ ብሶቴን፣ ሀዘኔን ገለጽኩኝ፤የውስጤን መከፋት በብዕሬ ጻፍኩኝ።📖ረመዷን....t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
አልዘይርም!!❌~ዒድ የደስታ፣ የፍቅር እና የዝምድና መቀጠያ ታላቅ ዕለት ነው። በዚህ ዕለት ዘመድ አዝማድን መጎብኘትና መጠ...
አልዘይርም!!❌~ዒድ የደስታ፣ የፍቅር እና የዝምድና መቀጠያ ታላቅ ዕለት ነው። በዚህ ዕለት ዘመድ አዝማድን መጎብኘትና መጠየቅ ትልቅ ምንዳ ያለው ተግባር ነው።ሆኖም ግን፣ ደስታችንን ፍጹም የሚያደርገው የአላህን ህግጋት ጠብቀን ስንገኝ ብቻ ነው።ብዙዎቻችን በዝምድና ሰበብ የምንፈጽመው ትልቁ ስህተት አጅነቢይ (መጋባት የሚፈቀድላቸው) ከሆኑ ዘመዶች ጋር መጨባበጥ ነው።ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦«ከእናንተ አንዳችሁ የማይፈቀድለትን ሴት ከመንካት ይልቅ በብረት ወስፌ ጭንቅላቱ ቢወጋ ይሻለዋል።»(ጦብራኒ ዘግበውታል)።ይህ ማስጠንቀቂያ ጉዳዩ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳየናል። ዒድ ዝምድናን የምንቀጥልበት እንጂ አላህን የምናምጽበት ቀን መሆን የለበትም።✅እነዚህን ዘመዶቻችንን መጨባበጥና ከፊታቸው ሂጃብ ማውለቅ ይፈቀዳል፦✅ወላጆችና አያቶች✅ወንድምና እህቶች✅የወንድምና የእህት ልጆች✅የራስ አክስትና አጎት (የአባትና የእናት ወንድም/እህቶች)✅የጡት ዘመዶች❌መጨባበጥ በጥብቅ የተከለከለባቸው (አጅነቢዮች)፦✋የአክስትና የአጎት ልጆች (በብዛት የሚዘናጋበት)✋የባል ወንድም ወይም የሚስት እህት✋የወንድም ሚስት ወይም የእህት ባል✋ጎረቤቶችና የራቁ ዘመዶችበዘመድ ጥየቃ ወቅት ሰዎች እጃቸውን ሲዘርጉልን ባለመጨባበጣችን ቅር ይላቸዋል ብለን ማሰብ የለብንም። ከአላህ ቁጣ የሰዎችን ቅሬታ መምረጥ ይሻላል።t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
📅6 ቀን ብቻ...💾ረመዷን ሲሄድ «ስንቄን ሰብስቤ አበቃሁ» አንልም፤ ይልቁንም ያገኘነውን ይዘን ጉዟችንን እንቀጥላለን። ም...
📅6 ቀን ብቻ...💾ረመዷን ሲሄድ «ስንቄን ሰብስቤ አበቃሁ» አንልም፤ ይልቁንም ያገኘነውን ይዘን ጉዟችንን እንቀጥላለን። ምክንያቱም አማኝ በዚህች ዓለም ላይ እውነተኛ ዕረፍት የለውም፤ ዕረፍቱ ከአንዱ መልካም ሥራ ወደ ሌላው መሸጋገር ብቻ ነው።የአላህ እዝነቱ ሰፊ ነው፤ በስድስት ቀን ጥረት የዓመት ሙሉ ፆም ምንዳን አዘጋጅቶልናል።የአላህ መልዕክተኛ እንደነገሩን፦ «ረመዷንን ፆሞ ስድስት የሸዋል ቀናትን ያስከተለ፣ ዓመቱን ሙሉ (365 ቀን) እንደፆመ ይቆጠርለታል።» ብለውናል።ጥቂት ድካም፣ ለብዙ ምንዳ!ስለዚህ ነገን በፆም እንጀምር። እያረፍንም ይሁን ተከታትለን፣ የዓመት ሙሉ ምንዳችንን አንጣ።~t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
❗️❗️❗️❗️❗️👍ቲክቶክ የምትጠቀሙ ካላችሁ አዲሱን የቲክቶክ (TikTok) ገፃችንን ፎሎው በማድረግ አብራችሁን እንድትዘል...
❗️❗️❗️❗️❗️👍ቲክቶክ የምትጠቀሙ ካላችሁ አዲሱን የቲክቶክ (TikTok) ገፃችንን ፎሎው በማድረግ አብራችሁን እንድትዘልቁ እንጋብዛችኋለን። የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ለመልካም ነገር እንጠቀምበት!📱የቲክቶክ አድራሻችን፦🔗https://www.tiktok.com/@sle_qelbachn1?_r=1&_t=ZS-94vQ2iUC5pY
❗️❗️❗️❗️❗️👍ቲክቶክ የምትጠቀሙ ካላችሁ አዲሱን የቲክቶክ (TikTok) ገፃችንን ፎሎው በማድረግ አብራችሁን እንድትዘል...
❗️❗️❗️❗️❗️👍ቲክቶክ የምትጠቀሙ ካላችሁ አዲሱን የቲክቶክ (TikTok) ገፃችንን ፎሎው በማድረግ አብራችሁን እንድትዘልቁ እንጋብዛችኋለን። የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ለመልካም ነገር እንጠቀምበት!📱የቲክቶክ አድራሻችን፦🔗https://www.tiktok.com/@sle_qelbachn1?_r=1&_t=ZS-94vQ2iUC5pY
❗️❗️❗️❗️❗️👍ቲክቶክ የምትጠቀሙ ካላችሁ አዲሱን የቲክቶክ (TikTok) ገፃችንን ፎሎው በማድረግ አብራችሁን እንድትዘል...
❗️❗️❗️❗️❗️👍ቲክቶክ የምትጠቀሙ ካላችሁ አዲሱን የቲክቶክ (TikTok) ገፃችንን ፎሎው በማድረግ አብራችሁን እንድትዘልቁ እንጋብዛችኋለን። የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ለመልካም ነገር እንጠቀምበት!📱የቲክቶክ አድራሻችን፦🔗https://www.tiktok.com/@sle_qelbachn1?_r=1&_t=ZS-94vQ2iUC5pY
❗️❗️❗️❗️❗️👍ቲክቶክ የምትጠቀሙ ካላችሁ አዲሱን የቲክቶክ (TikTok) ገፃችንን ፎሎው በማድረግ አብራችሁን እንድትዘል...
❗️❗️❗️❗️❗️👍ቲክቶክ የምትጠቀሙ ካላችሁ አዲሱን የቲክቶክ (TikTok) ገፃችንን ፎሎው በማድረግ አብራችሁን እንድትዘልቁ እንጋብዛችኋለን። የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ለመልካም ነገር እንጠቀምበት!📱የቲክቶክ አድራሻችን፦🔗https://www.tiktok.com/@sle_qelbachn1?_r=1&_t=ZS-94vQ2iUC5pY
❗️❗️❗️❗️❗️👍ቲክቶክ የምትጠቀሙ ካላችሁ አዲሱን የቲክቶክ (TikTok) ገፃችንን ፎሎው በማድረግ አብራችሁን እንድትዘል...
❗️❗️❗️❗️❗️👍ቲክቶክ የምትጠቀሙ ካላችሁ አዲሱን የቲክቶክ (TikTok) ገፃችንን ፎሎው በማድረግ አብራችሁን እንድትዘልቁ እንጋብዛችኋለን። የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ለመልካም ነገር እንጠቀምበት!📱የቲክቶክ አድራሻችን፦🔗https://www.tiktok.com/@sle_qelbachn1?_r=1&_t=ZS-94vQ2iUC5pY
🎧ይህንን የቁርኣን አንቀፅ ስሰማው ልቤ ይረጋጋል፣ ተስፋዬም ይለመልማል። እስቲ ቆም ብለሽ አድምጪው... የሰይዳና ኢብራሂም...
🎧ይህንን የቁርኣን አንቀፅ ስሰማው ልቤ ይረጋጋል፣ ተስፋዬም ይለመልማል። እስቲ ቆም ብለሽ አድምጪው... የሰይዳና ኢብራሂም ባለቤት ሳራ በተስፋ መቁረጥና በግርምት መሃል ሆና የነገረችውንና የተመለሰላትን ቃል ተመልከቺ፦قَالَتْ يَا وَيْلَتَىٰ أَأَلِدُ وَأَنَا عَجُوزٌ وَهَٰذَا بَعْلِي شَيْخًا ۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيْءٌ عَجِيبٌ (72) قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ (73)❝እሷም አለች፦ ወዮልኝ! እኔ አሮጊት፣ ይሄም ባሌ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን? ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው!❞❝(መላእክቱም) አሏት፦ «በአላህ ስራ ትገረሚያለሽን? የአላህ እዝነትና በረከቶቹ በእናንተ በቤተሰቦቹ ላይ ይሁን፤ እርሱ ምስጉንና ክቡር ነውና።’❞(ሱረቱ ሁድ፡ 72-73)ውድ እህቴ ሆይ!✅«እድሜዬ ሄደ፣ የሚጠይቀኝና የሚያገባኝ አገኝ ይሁን?» ብለሽ በጭንቀት ለምታለቅሺው...✅«መውለድ ፈልጌ ማህፀኔ ዝም አለ፣ አመታቱ ነጎዱ፣ተስፋ ቆረጥኩ» ለምትይው...ይህ አምላካዊ ቃል ላንቺም ጭምር ነው!ሳራ ተስፋ ቆርጣ ነበር። የእድሜዋ መግፋትና የሰውነትዋ መድከም ለልጅ የመታጨት እድሏን የጨረሰች አስመስሎባት ነበር። ነገር ግን የአጽናፈ ዓለሙ ጌታ ሰበብን ሳይሆን ትእዛዙን ነው የሚከተለው።መላእክቱ የሰጧት መልስ ዛሬም ላንቺ ይሰራል፦ «አተዕጀቢነ ሚን አምሪላህ? - በአላህ ስራ ትገረሚያለሽን?»🟢እድሜሽ የፈለገ ቢገፋ፣ የአላህ እዝነት ካንቺ ቀደም ይላል።🟢በሮች ሁሉ ቢዘጉ፣ እርሱ ያልታሰበ በር ይከፍትልሻል።ይህንን አያ ስታደምጪ ልብሽ ይርጋ። አላህ ላንቺም «አትገረሚ፣ የእኔ እዝነት ከሁሉ በላይ ነው» እያለሽ ነው። ተስፋ አትቁረጪ!~t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
😀ተለቀቀ…የ ሙኽተሶር አድ-ዳእ ወአድ-ደዋእ የማጠቃለያ ፈተና ውጤት!በዚህ የኪታብ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ላይ በአጠቃ...
😀ተለቀቀ…የ ሙኽተሶር አድ-ዳእ ወአድ-ደዋእ የማጠቃለያ ፈተና ውጤት!በዚህ የኪታብ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ላይ በአጠቃላይ610ተማሪዎች ተሳትፈዋል። ለተፈታኞች የቀረበው ፈተና ከ100 የታሰበ ሲሆን፣ የኪታቡንኢጃዛለማግኘት ዝቅተኛው የማለፊያ ነጥብ 70 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቀምጧል።በዚህ ላይ የተዘረዘሩት ውጤቶች ለኢጃዛ ብቁ የሆኑትንና 70 ነጥብና ከዚያ በላይ ያመጡ ተፈታኞችን ዝርዝር የያዘ ነው።t.me/Sle_qelbachn1
ውዷ እህቴ ሆይ!የሰው ልጅ በስሜትና በምክንያት መካከል በሚወጠርበት ጊዜ የሚሰማው ጭንቀት ቀላል አይደለም።ስሜትሽን በሚገባ...
ውዷ እህቴ ሆይ!የሰው ልጅ በስሜትና በምክንያት መካከል በሚወጠርበት ጊዜ የሚሰማው ጭንቀት ቀላል አይደለም።ስሜትሽን በሚገባ እረዳሻለሁ።ሆኖም ግን ትዳር የጥቂት ቀናት የፍቅር ስሜት ማጣጣም ሳይሆን፣ የእድሜ ልክ ጉዞ፣ የትውልድ ግንባታና የዱንያና አኺራ ስኬት መሠረት በመሆኑ ነገሮችን ከስሜት ወጣ ብለሽ በሰከነ መንፈስ እንድታያቸው እመክርሻለሁ።🩵እህቴ ሆይ! «ፍቅር እውር ነው» የሚባለው አባባል ዝም ብሎ የተፈጠረ አይደለም። በፍቅር የተለከፈ ልብ የሚወደውን ሰው እንከን ማየት ይሳነዋል። አንቺ ዛሬ እሱ ላይ የምታዪው ያንቺን ፍላጎት የሚያሟላውን ቆንጆ ጎኑን ብቻ ሊሆን ይችላል።ቤተሰቦችሽ ግን ካንቺ በተሻለ የሕይወት ተሞክሮ፣ ካንቺ በበሰለ እይታና ከስሜት ነፃ በሆነ መንገድ ነገሮችን የማየት ዕድል አላቸው።ለአፍታ ቆም በዪና እነዚህን ጥያቄዎች ራስሽን ጠይቂ፦☑የመረጥሽው ሰው ከዲኑ አንፃር የት ነው ያለው?የአላህን መብት የማይጠብቅ፣ ሶላቱን የማይጠነቅቅና አላህን የማይፈራ ሰው እንዴት ላንቺ ታማኝ ይሆናል? ለአላህ ያልታመነ ፍጡር ለፍጡር አይታመንም።☑ቤተሰቦቹስ እነማን ናቸው?ሰው የሚበቅልበት ማህበረሰብና ቤተሰብ ማንነቱን ይቀርጹታል። ቤተሰቦችሽ «አይሆንም» ሲሉ ስለ ግለሰቡ ብቻ ሳይሆን ስለሚመጣበት አካባቢና አስተዳደግ ጭምር ስጋት ኖሯቸው ሊሆን ይችላል።☑ሰፈርና ጎረቤት ስለ እሱ ምን ይላሉ?የአንድ ሰው እውነተኛ ማንነቱ የሚታወቀው አብረውት በሚኖሩ፣ በሚገበያዩትና በቅርብ በሚያውቁት ሰዎች ምስክርነት ነው። ስሜትሽ የጋረደብሽን እውነት እነሱ ሊያዩት ይችላሉ።🌟ውዷ እህቴ!ቤተሰቦችሽ ላንቺ ክፉ አይመኙም። ካንቺ በላይ የሚወድሽና ላንቺ የሚጨነቅ ከወላጆችሽ በላይ ማንም የለም። እነሱ ሌላ ሰው ደጋግመው የሚያመጡልሽ ካለሽበት የስሜት እስር አውጥተው በሰከነ መንገድ እንድታስቢ ለማድረግ ካላቸው ጉጉት የተነሳ ሊሆን ይችላል።አንቺ የመረጥሽው ሰው ካንቺ ጋር ብቻ ሳይሆን ነገ ከቤተሰቦችሽ ጋር ተስማምቶ የሚኖር፣ አንቺን የሚያከብርና ቤተሰብሽን የሚያስከብር መሆኑን ማረጋገጥ አለብሽ። በትዳር ውስጥ ከፍቅር በስተጀርባ ትልቅ ኃላፊነት አለ። ዛሬ የምታዪው ፍቅር ነገ የኑሮ ጫና ሲመጣ፣ የልጆች ሃላፊነት ሲኖርና ችግሮች ሲከሰቱ ሊቀንስ ይችላል፤ ያኔ ትዳሩን አጽንቶ የሚያቆየው የሰውየው ማንነት፣ አኽላቅ እና ዲኑ ብቻ ነው።ስለዚህ የኔ ምክር...✅ኢስቲኻራ አድርጊ: ከአላህ የተሻለውን እንድመርጥልች ጠይቂ። የመረጥሽው ሰው ለዲንሽም ለዱንያሽም ምርጥ ከሆነ አላህ የቤተሰቦችሽን ልብ እንዲያለሰልስልሽ ለምኚ። ካልሆነ ግን በሰላም እንዲያርቅልሽ ዱዓ አድርጊ።✅ለቤተሰቦችሽ ዕድል ስጪ: እነሱ የሚያመጡትን ሰው ጭራሽ «አልፈልግም» ከማለትሽ በፊት፣ በምን መስፈርት እንደመረጡትና ምን እንደታያቸው ለማወቅ ሞክሪ። ምናልባት አንቺ ስሜት ውስጥ ሆነሽ ያልታየሽ ትልቅ ቁምነገር እነሱ ጋ ይኖር ይሆናል።✅በግልጽ ተወያዩ: የምትወጂውን ሰው ቤተሰቦችሽ ለምን እንደማይፈልጉት በዝርዝር ጠይቂያቸው። ምክንያታቸው ሃይማኖታዊ ወይም ስነ-ምግባራዊ ከሆነ፣ ስሜትሽን ገታ አድርገሽ ለእውነታው እጅ ስጪ። ፍቅርን ተከትለሽ ወላጆችሽን አታስቀይሚ፤ የወላጅ ምርቃት የሌለበት ትዳር በረካው አጠራጣሪ ነው።አስታውሺ! ትዳር ማለት የአንድ ቀን ድግስ ሳይሆን የዘላለም ኑሮ ነው። ዛሬ በፍቅር አይን ያየሽው ሰው ነገ በትዳር ውስጥ ስታዪው ሌላ ሰው ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ምርጫሽ በስሜት ላይ ሳይሆን በእውቀት፣ በምክንያትና በአላህ ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ይሁን።አላህ ለዲንሽና ለኑሮሽ የሚበጀውን ትክክለኛውን ምርጫ ይምረጥልሽ። ቤተሰቦችሽንም አንቺንም በሚያስደስት መንገድ ይቋጭልሽ።✒️ወንድምሽ አቡ ሱፍያን➡t.me/Sle_qelbachn1➡️t.me/Sle_qelbachn1
ዕድሉ የ3 ሰው ብቻ ነው—ዝግጁ ናችሁ?በግራፊክስ ዲዛይንና በቪዲዮ ኤዲቲንግ ስልጠና ስሙ የናኘውዲናር ቴክኖሎጂ፣ ለ14ኛ ዙ...
ዕድሉ የ3 ሰው ብቻ ነው—ዝግጁ ናችሁ?በግራፊክስ ዲዛይንና በቪዲዮ ኤዲቲንግ ስልጠና ስሙ የናኘውዲናር ቴክኖሎጂ፣ ለ14ኛ ዙር ምዝገባውን ማጠናቀቁን ተከትሎ ለእኔ ሦስት (3) የነፃ የትምህርት ዕድሎችን በስጦታ አበርክቶልኛል።እኔም ይህን ታላቅ ዕድል ለእናንተ ለውድ ቤተሰቦቼ ላካፍላችሁ ወስጃለሁ። ዕድሉን የሚገባቸውን ሦስት ዕድለኞች ለመለየት ጥቂት የፈተና ጥያቄዎችን አዘጋጅቻለሁ።ፈጥነውበትክክል ለሚመልሱ ሦስት ተወዳዳሪዎች እንደ ፍላጎታቸው 'የግራፊክስ ዲዛይን' ወይም 'የቪዲዮ ኤዲቲንግ' ሙሉ ስልጠናውን በነፃ የሚከታተሉ ይሆናል።🕐ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ እንገናኝ!t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
🎁የልባችንን በሽታ የምንታከምበት አዲስ የብስራት ዜና!🧡የደረቀ ልብን የሚያለመልም፣ የዛለች ነፍስን የሚያድስ ልዩ የቂርኣት...
🎁የልባችንን በሽታ የምንታከምበት አዲስ የብስራት ዜና!🧡የደረቀ ልብን የሚያለመልም፣ የዛለች ነፍስን የሚያድስ ልዩ የቂርኣት ፕሮግራም እነሆ ሊጀምር ነው!የሰው ልጅ አካል ጤነኛ የሚሆነው ቀልቡ ጤነኛ ሲሆን ብቻ ነው፤ ልብ ሲደርቅ ግን ሕይወት ትርጉም ታጣለች።📚የኪታቡ ስም፦ذَمُّ قَسْوَةِ الْقَلْبِ وَذِكْرُ أَسْبَابِهَا وَمَا تَزُولُ بِهِ(የቀልብ መድረቅ አደገኝነት፣ መንስኤውና መፍትሔው)📝ዝግጅት፦ታላቁ ዓሊም አል-ኢማም ኢብኑ ረጀብ (ረሒመሁላህ)🎙በኡስታዝ፦ዐብዱ ረዛቅ አል-ባጂ (ሐፊዘሁላህ)🗓የመጀመሪያ ቀን፦ሐሙስ ሚያዚያ 15 ይጀምራል-⏰የደርሱ ቀናት፦ዘወትር ረቡዕ እና ሐሙስ-ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ-📚የኪታቡን PDF ለማገኘት ይጫኑኝ!⚡️ትምህርቱ በቀጥታ ስርጭት (Live) የሚሰጥበት ቻናል፦👇🔗https://t.me/Sle_qelbachn1🌐https://t.me/Sle_qelbachn1ለሌሎችም በማጋራት የዚህ ታላቅ ኸይር ተካፋይ ይሁኑ!
🪶ውድ እህቴ ሆይ! የልብሽን ስብራት፣ የነፍስሽን ሲቃና የህሊናሽን ቁስል ቃላት ሊገልጹት አይችሉም። አንቺ ራስሽን ጠብቀሽ፣...
🪶ውድ እህቴ ሆይ! የልብሽን ስብራት፣ የነፍስሽን ሲቃና የህሊናሽን ቁስል ቃላት ሊገልጹት አይችሉም። አንቺ ራስሽን ጠብቀሽ፣ በሃላል መንገድ ትዳር መስርተሽ፣ በናፍቆት ለጠበቅሽው ባልሽ የሰጠሽው ትልቁ ስጦታ ታማኝነትሽን ነበር። ነገር ግን ያሰብሽው የፍቅር አቀባበል ሳይሆን የክስ መዓት በወረደብሽ ጊዜ ዓለም ጨልማብሻለች።አይዞሽ እህቴ! የሰው ልጅ ባያምንሽም፣ የሰማይና የምድር ጌታ የሆነው አላህ ንፅህናሽን ያውቃል። እርሱ እውነቱን አውቆ ዝም ማለቱ ለጊዜው ቢከብድሽም፣ መጨረሻው ግን የጥሩዎች ነው።🔴ወንድሜ ሆይ! ቆም ብለህ አስብ። ትዳር የሚገነባው በደም ጠብታ ሳይሆን በተቅዋ እና በአማና ላይ ነው። አንዲት ሴት በመጀመሪያ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ወቅት ደም ስላላፈሰሰች ብቻ ዝሙት ፈጽማለች ብሎ መደምደም ትልቅ ስህተት ብቻ ሳይሆን በኢስላም ታላቅ ወንጀል (ቀዝፍ) ነው።💊የህክምናው ዓለምና የተፈጥሮ ህግ የሚነግሩን እውነታ አለ፦ ሁሉም የሴት ልጅ የድንግልና ሽፋን አንድ አይደለም። በከባድ ስራ የዛለ፣ በገጠር አቀበትና ቁልቁለት የደከመ፣ በተፈጥሮው የመለጠጥ ባህሪ ያለው ሽፋን ደም ላያፈስ ይችላል። ታዲያ ይህቺን አማኝና ታማኝ ሚስትህን«ደም የለሽም» ብለህ ስትወነጅላት፣ በሰማይ ቤቱ መዝገብ ላይ ጨዋ ሴትን በዝሙት መወንጀል የሚል ታላቅ ወንጀል እየጻፍክ መሆንህን አላስተዋልክም?🦋ይህቺ እህት ለ7 ዓመታት በሰው ሀገር በከባድ ስራ መቆየቷንና በገጠር ማደጓን ነግራሃለች። ይህ ብቻውን ለሽፋኑ መጥፋት ወይም መላላት በቂ ምክንያት ሊሆን ይችላል።ኢስላም አንዲትን ሙስሊም ሴት በዝሙት ለመክሰስ 4 ታማኝ ምስክሮችን ይፈልጋል። እነዚህ ምስክሮች በሌሉበት "ደም አላየሁም" በሚል ግምት ብቻ ክብርን ማዋረድ አላህን መዳፈር ነው።ወንድሜ ሆይ! ሦስት ዓመት ሙሉ በታማኝነት የጠበቀችህን፣ ድኗንና አህላቋን የምታውቅላትን ሚስትህን በጥርጣሬ ደመና አታጥቁራት። ፍቅር በመተማመን ላይ ካልቆመ ፍቅር አይደለም። ንፅህና በልብና በተግባር እንጂ በጨርቅ ላይ በሚፈስ ጠብታ አይለካም።ውድ እህቴ፦✅አንቺ አላህ ዘንድ ንፁህ ከሆንሽ የባልሽ አለማመን አንቺን "ዛኒያ" አያደርግሽም። ክብሯን ለባሏ የጠበቀች ሴት አላህ ዘንድ ትልቅ ቦታ አላት።✅እሱን ለማስረዳት ጥረት አድርገሻል። ካልተቀበለሽና ስድብና ውርደትን ምርጫው ካደረገ፣ አላህ ካንቺ የተሻለ የሚያውቅልሽ ነገር ይኖራል። ትዳር መከባበር የሌለበት እስር ቤት ሊሆን አይገባም።✅ዱዓ አድርጊ።«አላህ ሆይ! እውነቱን አንተ ታውቃለህና አንተው ፍረድልኝ»ብለሽ ለጌታሽ ንገሪው። ልቡን እንዲያለዝብልሽ ወይም ካንቺ የተሻለውን እንዲተካልሽ ለምኚው።ሴት ልጅን እንደ ቁስ ሳይሆን እንደ ሰው እዩዋት። ትዳር ውስጥ በጥርጣሬ መግባት የሰይጣን በር መክፈት ነው። ብዙ እህቶቻችን በተፈጥሮአዊ ምክንያት ደም ስላልታየ ብቻ ህይወታቸው ሲቃወስ ማየት እጅግ ያማል።እህቴ ሆይ!አላህ ንፅህናሽን ያውቃል። ሰው ባይረዳሽም አላህ ግን አይተውሽም።አብሽሪ!!~t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
📔ማሳሰቢያ!የ ሙኽተሶር አዳእ ወደዋእ የመጨረሻውን ፈተና አልፋችሁ ኢጃዛ የፀደቀላችሁ እህቶችና ወንድሞች፤ በኢሜይል አድራሻ...
📔ማሳሰቢያ!የ ሙኽተሶር አዳእ ወደዋእ የመጨረሻውን ፈተና አልፋችሁ ኢጃዛ የፀደቀላችሁ እህቶችና ወንድሞች፤ በኢሜይል አድራሻችሁ ለመላክ ጥረት ብናደርግም በተለያዩ ምክንያቶች ያልደረሳችሁና የተመለሱብን ስላሉ የሚከተለውን መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ ኢጃዛችሁን በፍጥነት ተቀበሉ።1⃣በፒዲኤፍ (PDF) ዝርዝሩ ላይስማችሁ መኖሩን መጀመሪያ ያረጋግጡ።2⃣ስማችሁ በዝርዝሩ ውስጥ ካለ፣ሙሉ ስማችሁን በ አማርኛ ብቻበሚከተለው አድራሻ ይላኩልን፦💭👉@Eijaza20⚠️ጥብቅ ማሳሰቢያ፦ስራን ለማቀላጠፍ ሲባል ከሙሉ ስም ውጭ ምንም ዓይነት ሰላምታም ሆነ ሌላ ተጨማሪ ጽሁፍም ሆነ ሐሳብአንዳትጽፉበትህትና እንጠይቃለን። ስማችሁን ብቻ በላካችሁልን መሰረት ኢጃዛችሁን የምንልክላችሁ ይሆናል።
ወንጀልን ለመተው እየታገልኩ ራሴን መልሼ እዛው ረግረግ ውስጥ አገኘዋለሁ... ከራሴ ጋር ተሸነፍኩ! የሚል የልብ ጩኸት። የ...
ወንጀልን ለመተው እየታገልኩ ራሴን መልሼ እዛው ረግረግ ውስጥ አገኘዋለሁ... ከራሴ ጋር ተሸነፍኩ! የሚል የልብ ጩኸት። የተሰበረች ነፍስ የምታሰማው የድረሱልኝ ጥሪና የተስፋ ብርሃን የተሞላበት ምላሽ። እስከመጨረሻው አድምጡት።~t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
የምስራች📶💡💡💡💡💡💡💡💡ተጀመረ🌟ተጀመረ ተጀመረ✅🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥1️⃣5️⃣ኛው ዙርየግራፊክ ዲዛይን እና የቪዲዮ ኢዲቲንግ ስልጠና...
የምስራች📶💡💡💡💡💡💡💡💡ተጀመረ🌟ተጀመረ ተጀመረ✅🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥1️⃣5️⃣ኛው ዙርየግራፊክ ዲዛይን እና የቪዲዮ ኢዲቲንግ ስልጠና ምዝገባ ተጀመረ📣ይህን ስልጠና በዲናር ቴክኖሎጂ ለ1️⃣5️⃣ኛ ጊዜ በሞባይሎቻችን ብቻ ተጠቅመን በቂ ችሎታ እና ልምድ ከሰርተፍኬት ጋር የምናገኝበትን ስልጠና በተመጣጣኝ ዋጋ አዘጋጅቶልናልይመዝገቡ📣ይመዝገቡ📣⚫የዚህ ዙር ምዝገባ የሚቆየው ለ 2 ቀን ብቻ ነው🔊✅ለመመዝገብበዚህ ያናግሩን⬇️t.me/dinarmzgeba
የምስራች📶💡💡💡💡💡💡💡💡ተጀመረ🌟ተጀመረ ተጀመረ✅🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥1️⃣5️⃣ኛው ዙርየግራፊክ ዲዛይን እና የቪዲዮ ኢዲቲንግ ስልጠና...
የምስራች📶💡💡💡💡💡💡💡💡ተጀመረ🌟ተጀመረ ተጀመረ✅🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥1️⃣5️⃣ኛው ዙርየግራፊክ ዲዛይን እና የቪዲዮ ኢዲቲንግ ስልጠና ምዝገባ ተጀመረ📣ይህን ስልጠና በዲናር ቴክኖሎጂ ለ1️⃣5️⃣ኛ ጊዜ በሞባይሎቻችን ብቻ ተጠቅመን በቂ ችሎታ እና ልምድ ከሰርተፍኬት ጋር የምናገኝበትን ስልጠና በተመጣጣኝ ዋጋ አዘጋጅቶልናልይመዝገቡ📣ይመዝገቡ📣⚫የዚህ ዙር ምዝገባ የሚቆየው ለ 2 ቀን ብቻ ነው🔊✅ለመመዝገብበዚህ ያናግሩን⬇️t.me/dinarmzgeba
የምስራች📶💡💡💡💡💡💡💡💡ተጀመረ🌟ተጀመረ ተጀመረ✅🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥1️⃣5️⃣ኛው ዙርየግራፊክ ዲዛይን እና የቪዲዮ ኢዲቲንግ ስልጠና...
የምስራች📶💡💡💡💡💡💡💡💡ተጀመረ🌟ተጀመረ ተጀመረ✅🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥1️⃣5️⃣ኛው ዙርየግራፊክ ዲዛይን እና የቪዲዮ ኢዲቲንግ ስልጠና ምዝገባ ተጀመረ📣ይህን ስልጠና በዲናር ቴክኖሎጂ ለ1️⃣5️⃣ኛ ጊዜ በሞባይሎቻችን ብቻ ተጠቅመን በቂ ችሎታ እና ልምድ ከሰርተፍኬት ጋር የምናገኝበትን ስልጠና በተመጣጣኝ ዋጋ አዘጋጅቶልናልይመዝገቡ📣ይመዝገቡ📣⚫የዚህ ዙር ምዝገባ የሚቆየው ለ 2 ቀን ብቻ ነው🔊✅ለመመዝገብበዚህ ያናግሩን⬇️t.me/dinarmzgeba
ለመሆኑ ከአላህ ቃል በላይ የሰውን ልጅ ነፍስ ከውጥረት አላቆ፣ ልብን በሰላምና በእርጋታ የሚያጠግብ ምን ሌላ ነገር አለ?!...
ለመሆኑ ከአላህ ቃል በላይ የሰውን ልጅ ነፍስ ከውጥረት አላቆ፣ ልብን በሰላምና በእርጋታ የሚያጠግብ ምን ሌላ ነገር አለ?!----۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ❝በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡❞◈ሱረቱ አል-ዙመርt.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
የምስራች📶💡💡💡💡💡💡💡💡ተጀመረ🌟ተጀመረ ተጀመረ✅🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥1️⃣6️⃣ኛው ዙርየግራፊክ ዲዛይን እና የቪዲዮ ኢዲቲንግ ስልጠና...
የምስራች📶💡💡💡💡💡💡💡💡ተጀመረ🌟ተጀመረ ተጀመረ✅🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥1️⃣6️⃣ኛው ዙርየግራፊክ ዲዛይን እና የቪዲዮ ኢዲቲንግ ስልጠና ምዝገባ ተጀመረ📣ይህን ስልጠና በዲናር ቴክኖሎጂ ለ1️⃣6️⃣ኛ ጊዜ በሞባይሎቻችን ብቻ ተጠቅመን በቂ ችሎታ እና ልምድ ከሰርተፍኬት ጋር የምናገኝበትን ስልጠና በተመጣጣኝ ዋጋ አዘጋጅቶልናልይመዝገቡ📣ይመዝገቡ📣⚫የዚህ ዙር ምዝገባ የሚቆየው ለ 3 ቀን ብቻ ነው🔊ክረምቱን እነዚህን ወሳኝ ኮርሶችን በመውሰድ ይጠቀሙበት✅ለመመዝገብበዚህ ያናግሩን⬇️t.me/dinarmzgeba
የእውነተኛ ተውበት ማሳያ...የተቡክ ዘመቻ አልፎ ነቢዩ (ﷺ) ወደ መዲና ተመለሱ፡፡ ሙናፊቆች እየመጡ ሀሰተኛ ምክንያት እየ...
የእውነተኛ ተውበት ማሳያ...የተቡክ ዘመቻ አልፎ ነቢዩ (ﷺ) ወደ መዲና ተመለሱ፡፡ ሙናፊቆች እየመጡ ሀሰተኛ ምክንያት እየደረደሩ ማሉ፤ ነቢዩም (ﷺ) ውጫዊ ሰበባቸውን ተቀብለው ይቅር አሏቸው፡፡ተራው የካዕብ ኢብኑ ማሊክ ደረሰ፡፡ ካዕብ እንደ ሙናፊቆቹ ውሸት መደርደር፣ ማምለጫ መፈለግ ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን እርሱ ለአላህና ለረሱሉ (ﷺ) እውነተኛ መሆንን መረጠ፡፡ ወደ ነቢዩ (ﷺ) ቀረብ አለና፡ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምንም ዓይነት ሰበብ የለኝም፤ ከዚህ በፊት እንደ አሁኑ ተመችቶኝ አያውቅም» በማለት እውነቱን ተናገረ፡፡ነቢዩም (ﷺ)»ይህ ሰውማ እውነቱን ተናግሯል» አሉ፡፡ ነገር ግን እውነተኛነቱ ወዲያውኑ ምቾትን አላመጣለትም፤ ይልቁኑ ትልቅ ፈተናን እንጂ፡፡ አላህ ፍርዱን እስኪያወርድ ድረስ ነቢዩ (ﷺ) ማንም ሰው ከካዕብና ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር እንዳያወራ ከረረ ያለ እገዳጣሉ፡፡ያቺ ሰፊዋ መዲና በካዕብ ላይ ጠበበችበት፡፡ ምድር መረጋጋጫ አጣችለት፡፡ ሰላምታ የሚመልስለት፣ ቀና ብሎ የሚያየው ሰው ጠፋ፡፡ ለአምሳ ቀናት ሙሉ በፀፀት እሳት እየነደደ፣ ሌትና ቀን እምባውን እየዘራ ወደ ጌታው አለቀሰ፡፡ በዚህ መሃል የሻም ንጉስ የችግሩን ጊዜ ተጠቅሞ በደብዳቤ ሊያታልለውና ሊያሸፍተው ቢሞክርም፣ ካዕብ ግን ደብዳቤውን እሳት ውስጥ በመክተት ለአላህና ለረሱል ያለውን ታማኝነት አረጋገጠ፡፡በሃምሳኛው ቀን ንጋት ላይ፣ የሰማይና የምድር ጌታ የሆነው አላህ እውነተኛነታቸውን አውቆ፣ ከሰማያት በላይ ተውበታቸውን መቀበሉን የሚገልጽ አንቀጽ አወረደ፡የመዲና ተራሮች በደስታ ድምፅ አስተጋቡ! «ያ ካዕብ ሆይ! የምስራች!» የሚል ጩኸት መዲናን አናወጣት፡፡ ካዕብ በደስታ ብዛት ወዲያውኑ ለአላህ ሱጁድ ወረደ፡፡ ወደ መስጂድ ሲሮጥ ሰሐቦች በደስታ ከበውት እንኳን ደስ አለህ ይሉት ጀመር፡፡ ነቢዩም (ﷺ) ፊታቸው እንደ ጨረቃ በደስታ እያበራ፡ «እናቱ ከወለደችህ ጀምሮ ካለፉት ቀናት ሁሉ በበለጠ በላጭ በሆነው ቀን የምስራች!»አሉት፡፡ካዕብም በደስታ እያለቀሰ፡ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህ ያዳነኝ በእውነተኛነቴ ነው፤ ከእንግዲህም በህይወቴ እውነትን እንጂ አልናገርም» አለ፡፡አላህ የከዕብ አይነት ተውበት ይወፍቀን!t.me/Sle_qelbachn1t.me/Sle_qelbachn1
وَلَا تُخْزِنِي يَوْمَ يُبْعَثُونَበሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ፡፡يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَا...
وَلَا تُخْزِنِي يَوْمَ يُبْعَثُونَበሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ፡፡يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡»[سورة الشعراء]
ሐቂቃ የሰዎችን ልብ ለመግራትና ነፍስን ለመገሰጽ የተጻፉ በርካታ ኪታቦች አሉ። ነገር ግን የ ኢማም ኢብኑል ቀይም እና ኢማ...
ሐቂቃ የሰዎችን ልብ ለመግራትና ነፍስን ለመገሰጽ የተጻፉ በርካታ ኪታቦች አሉ። ነገር ግን የ ኢማም ኢብኑል ቀይም እና ኢማም ኢብኑል ጀውዚ ኪታቦች እኔ ጋር ያላቸው ቦታ ፈጽሞ የተለየ ነው።የእነርሱ ኪታቦች ተራ ምክሮች ብቻ አይደሉም፤ የሰውን ልጅ ውስጣዊ በሽታዎች ጠልቀው የሚመረምሩ፣ ለቆሰሉ ልቦች ፈውስ የሚሰጡ እና ስሜትን ሳይሆን አቅልንና ኢማንን የሚያነቁ ሕያው ማስተማሪያዎች ናቸው። አላህ በሰፊው እዝነቱ ይማራቸው!➠t.me/Sle_qelbachn1
ይገርመኛል ... የኔ ነገር አብዝቶ ይገርመኛል የትም ዞሬ ዞሬ ፤ የትም ጠፍቼ ቆይቼ መጥቼ አላህ ሆይ ማረኝ ስለው አለማፈ...
ይገርመኛል ... የኔ ነገር አብዝቶ ይገርመኛል የትም ዞሬ ዞሬ ፤ የትም ጠፍቼ ቆይቼ መጥቼ አላህ ሆይ ማረኝ ስለው አለማፈሬ ይገርመኛል።ኢላሂ ...የቱን ያህል ባጠፋም ከ አንተ ርቄ ላለመራቅ እየታገልኩ ነውና እገዘኝ!…አህህ አንተ ጌታዬ እኔ ባርያህ በመሆኔ እንዴት ዕድለኛ ነኝ!!ረሕማን የሚለዉን ሥምህን አስታወስኩኝና እዝነተህ ትዝ አለኝ፤ ከሰፊው ረሕመትህ ቦታ ካጣዉማ ሞቼ ትቢያ ሆኜ መቅረትን ተመኘሁ፡፡
ለዚህ ቪዲዮ እኔም ህያው ምስክር ነኝ! ሀቂቃ… ትዳር የሪዝቅና የበረካ በራፍ ነው።ሰራተኞች አሉኝ፤ ያገቡትም፣ ያላገቡትም...
ለዚህ ቪዲዮ እኔም ህያው ምስክር ነኝ! ሀቂቃ… ትዳር የሪዝቅና የበረካ በራፍ ነው።ሰራተኞች አሉኝ፤ ያገቡትም፣ ያላገቡትም፣ ልጆች ያላቸውም አሉ። የሁሉንም ወርሃዊ ደመወዝ እኔው ነኝ የምከፍለው፤ ክፍያቸውም በጣም ተቀራራቢ ነው። ነገር ግን እውነተኛው ልዩነት የሚታየው ደመወዝ ከተከፈለ በኋላ ባለው ህይወትነው!ያገቡት ሰራተኞቼ ያቺኑ የምከፍላቸውን ደመወዝ አብቃቅተው፣ ቤታቸውን መርተው፣ የልጆቻቸውን ፍላጎት አሟልተው በሰላም ሲኖሩበት፤ ላጤዎቹ ሰራተኞቼ ግን ገና ወሩ አጋማሽ ሳይደርስ «እባክህ የቀጣይ ወር ደመወዝ ቅድሚያ ስጠኝ» እያሉ ማንኳኳት ይጀምራሉ!--ሀሀ--እናላችሁ… በትዳር ውስጥ ያለው ሚስጥር የገንዘቡ ብዛት ሳይሆን የበረካው ስፋት ነው ወላሂ! ትዳር ትንሹን አብዝቶ፣ ጎደሎውንሞልቶ ያሳያል። ስለዚህ ያላገባችሁ… ከመበደር ወደ ማብቃቃት፣ ከላጤነት ወደ በረካው ጎጆ ተሻገሩ ለማለት ነው! 😉t.me/AbuSufiyan_Albenant.me/AbuSufiyan_Albenan
;قَالَ قَدْ أُجِيبَت دَّعْوَتُكُمَا'❝ዱዓችችሁ በእርግጥ ተሰምታለች፡፡❞—የሚል የምስራች የሚሰማበትን ...
;قَالَ قَدْ أُجِيبَت دَّعْوَتُكُمَا'❝ዱዓችችሁ በእርግጥ ተሰምታለች፡፡❞—የሚል የምስራች የሚሰማበትን ጊዜ አላህ ያቅርብላችሁ።ላንቃ እስከሚደርቅ በለቅሶና በዱዓ የለመናችሁት፣ ለዚሁ ጉዳይ ብላችሁ እንቅልፍ ያጣችሁበትና ልባችሁ የተሰበረበትን ጉዳይ ሁሉ..አላህዪ በሰመረ ውጤት ያሳካላችሁ!✈️⬜️ስለ ቀልባችን☑️➡️Share:t.me/Sle_qelbachn1
⚠️በጣም የሚያስፈራራኝ የቁርኣን አያህ፦«وَعَصَيْتُم مِّن بَعْدِ مَا أَرَاكُم مَّا تُحِبُّون...
⚠️በጣም የሚያስፈራራኝ የቁርኣን አያህ፦«وَعَصَيْتُم مِّن بَعْدِ مَا أَرَاكُم مَّا تُحِبُّونَ»(የምትወዱትን ካሳየኋችሁ በኋላ አመፃችሁ!) — [አል-ዒምራን፡ 152]በጭንቅ ቀን እጅህን ዘርግተህ፦❝ያ አላህ! ይህን ብቻ ፈፅምልኝ እንጂ ከእንግዲህ ዳግመኛ አልመለስበትም፤ ቃል እገባልሃለሁ!❞ ብለህ ስትለምነው የነበረውን ቀን አስታውስ።ጌታህ አዘነልህ፤ የለመንከውን ሰጠህ፤ ልብህ የተመኘውን አሳየህ፤ ጭንቅህን ገፈፈልህ።ነገር ግን... ገና ከእጁ የተቀበልከው ጸጋ ሳይቀዘቅዝ፣ የታበሰው እንባህ ሳይደርቅ፣ በዚያው በሰጠህ ኃይል፣ ጤና እና ጸጋእርሱን መልሰህ አመፃኸው! ያቺን የማልክባትን ወንጀል በጌታህ ፊት ደግመህ ተገበርካት።ከዚህ በላይ የሚያስፈራና የሚያሳፍር ታላቅ ክህደት አለን?! አንተ ከጌታህ 'የምትወደውን' ትቀበላለህ፤ እርሱ ግን ከአንተ'ሚጠላውን' ያገኛል!✈️⬜️ስለ ቀልባችን☑️➡️Share:t.me/Sle_qelbachn1
📓በለይላ ፍቅር ያበደው ሰው!(የመጅኑን ለይላ አስገራሚ ታሪክ)🎥ልዩ የቀጥታ ስርጭት (TikTok Live)✅ከ«መጅኑን ለይላ...
📓በለይላ ፍቅር ያበደው ሰው!(የመጅኑን ለይላ አስገራሚ ታሪክ)🎥ልዩ የቀጥታ ስርጭት (TikTok Live)✅ከ«መጅኑን ለይላ» ታሪክ የምንማራቸው ትልልቅ ቁምነገሮች፤✅ከሐራም ፍቅር ጋር የተያያዙ አንገብጋቢ ነጥቦችና አደጋዎች፤✅ልባችንን ካልተፈቀደ ሐራም ፍቅር እንዴት እንጠብቅ?፤✅በሐራም ፍቅር ለተያዙ ሰዎች ተግባራዊ የመውጫ መፍትሔዎች እና ሌሎች ነጥቦችን እንዳስሳለን...🗓ቀን፦እሁድ፣ ነሐሴ 17⏰ሰዓት፦ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ🎙️አቅራቢ፦ወንድም አቡ ሱፍያን🔠---በቲክ ቶክ---👇👇https://www.tiktok.com/@sle_qelbachn1?_r=1&_t=ZS-992wv4fSSc0
ኢብኑ ረጀብ رحمه الله እንዲህ ሲሉ ይናገራሉ፦አንድ ሰው በሌሊት ሰው በሌለበት ሜዳ ላይ አንዲትን ሴት በወንጀል ሊያባ...
ኢብኑ ረጀብ رحمه الله እንዲህ ሲሉ ይናገራሉ፦አንድ ሰው በሌሊት ሰው በሌለበት ሜዳ ላይ አንዲትን ሴት በወንጀል ሊያባብላት ሞከረ። እሷ ግን እምቢ አለች። እሱም፦ “ከዋክብት ብቻ እንጂ ማንም አያየንም” አላት። እሷም፦ “ታዲያ የእነርሱ ፈጣሪ የት አለ?” አለችው።ማለትም፦ አላህ እያየን ነው፤ ከእርሱ ምንም ነገር አይሰወርም ለማለት ፈልጋ ነው።አላህም እንዲህ ብሏል፦﴿أَلَمْ يَعْلَمْ بِأَنَّ اللَّهَ يَرَى﴾“እርሱ አላህ እንደሚያየው አያውቅምን?”አላህ እኛን ሁልጊዜ እንደሚያየን ማስታወስ ሰውን ከወንጀል ለመከልከልና ለመግታት በቂ ነው።
«በሶላቱ ላይ እነዚህ 6 አስፈሪ ምልክቶች የታዩበት ሰው የሙናፊቅ መለያ አለበት!» ይላሉ ኢብኑል ቀይም፦❶ስንፍና፦ ወደ ሶ...
«በሶላቱ ላይ እነዚህ 6 አስፈሪ ምልክቶች የታዩበት ሰው የሙናፊቅ መለያ አለበት!» ይላሉ ኢብኑል ቀይም፦❶ስንፍና፦ ወደ ሶላት በከበደ መንፈስ መነሳት።➋ይዩልኝ (ሪያዕ)፦ለሰው እይታና ሙገሳ መስገድ።❸ማዘግየት፦ሶላትን ከወቅቱ ማሳለፍ ወይም አዘግይቶ መስገድ።❹በ ፍጥነት መስገድ፦እህል እንደምትበላ ዶሮ መሬት እየነኩ ሩኩዕና ሱጁድን ማፍጠን።❺ዚክር ማሳነስ፦በሶላት ውስጥ አላህን በጥቂቱ እንጂ አለማስታወስ።❻ከጀመዓ መቅረት፦ያለ ምክንያት ለወንዶች የጀመዓ ሶላትን መተው።|✈️⬜️ስለ ቀልባችን☑️➡️Share:t.me/Sle_qelbachn1